Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, April 13, 2012

ክብርት አና ጎሜዝ የስዊድን ጋዜጠኞች እንዳይፈቱ እንቅፋት ሆነዋል ተባለ

Esat News

ኢሳት ዜና:-የስዊድን ጋዜጠኞችን ለማስፈታት የአውሮፓ ህብረት ወደ ኢትዮጵያ የላካቸው ሉዊስ ሚሸል፣ መለስ ዜናዊ ጋዜጠኞችን የማይፈታቸው በክብርት አና ጎሜዝ የተነሳ መሆኑን ለስራ ባልደረቦቻቸው መናገራቸውን ታማኝ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለኢሳት ገልጠዋል። መለስ ዜናዊ ጋዜጠኞችን ለመፍታት ይፈልጋል፣ ነገር ግን በውይይታችን ወቅት ደጋግሞ የሚያነሳው ስለ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው፤ እንደተረዳሁት ለጋዜጠኞቹ መፈታት እንቅፋት የሆነችው አና ጎሜዝ ናት በማለት መናገራቸው ታውቋል።

የመለስ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የአውሮፓ ፓርላማ አባሉ ሉዊስ ሚቸል ፣ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ከመለስ ዜናዊ ጋር መነጋገራቸው እንዲሁም በቃሊቲ የሚገኙ ጋዜጠኞችን መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከጉብኝታቸው በሁዋላም ጋዜጠኞቹ በሳምንታት ውስጥ በይቅርታ እንደሚፈቱ ገልጠዋል።

 ይሁን እንጅ የእርሳቸው መግለጫ በተሰጠ በማግስቱ አቶ በረከት ጋዜጠኞቹ እንደማይፈቱ ግልጽ ማድረጋቸው ይታወሳል። ሉዊስ ሚቸል ለጋዜጠኞች አለመፈታት ምክንያቱ መለስ ራሳቸው ናቸው ከማለት አና ጎሜዝ ናቸው ማለታቸው ብዙ ዲፐሎማቶችን ማስገረሙም ታውቛል። የስዊድን መንግስት በሉዊስ ሚቸል የዲፐሎማሲ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ አመኔታ ጥሎ እንደነበር ታውቋል።

No comments:

Post a Comment