Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, April 13, 2012

የሱዳኖች ጦርነት


Am 9.7.2011 wird Südsudan ein unabhängiger Staat.
የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ሁለቱን ሐገራት በሚያዋስነዉ ድንበር የጀመሩትን ዉጊያ እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የአፍሪቃ ሕብረት ጠየቁ።ሁለቱ ማሕበራት በየፊናቸዉ ባወጡት መግለጫ ሱዳኖች የሚያወዛግቧቸዉን ጉዳዮች በድርድር እንዲፈቱ አደራ ብለዋል።ማሕበራቱ የደቡብ ሱዳን ጦር በሐይል ከያዘዉ አወዛጋቢ ግዛት ለቅቆ እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ሰሜን ሱዳን የደቡብ ጠላቷ የሚቆጣጠረዉን ግዛትዋን ካለቀቀ በሐይል ለማስለቀቅ ዝታለች።የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪር ዛሬ እንዳሉት ግን ጦራቸዉ ከትናንት በስቲያ የያዘዉን ግዛት ለቅቆ አይወጣም።
በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጦራቸዉ ሒጂሊጅን የተቆጣጠረዉ የሰሜን ሱዳን ጦር ተኩስ ሥለከፈተበት ነዉ።የሰሜን ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ራሕማ መሐመድ ኦስማን እንዳስታወቁት ደግሞ የጁባ ጦር የሰሜን ሱዳንን ሰባ ኪሎ ሜትር ግዛት ወሯል። የሰሜንና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት ጦሮች በሁለቱ ሐገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ የገጡሙት ዉጊያ ብሶ ቀጥሏል።

የካርቱምና የጁባ ባለሥልጣናት ሕዝባቸዉ ከየጦሩ ጎን እንዲቆም በየፊናቸዉ እየጠየቁ ነዉ።የሰሜን ሱዳን መንግሥት ዛሬ እንዳስታወቀዉ የደቡብ ሱዳን ጦር፥ በደቡብ ሱዳን የሚደገፈዉ SPLA-N በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ አማፂ ቡድንና ጂም በሚል አፅሕሮቱ የሚጠራዉ የዳርፉር አማፂ ቡድን ለሰወስት ጥቃት ከፍተዉብኛል በማለት ይወነጅላል።ሁለቱ አማፂ ቡድናት ግን በዉጊያ አልተሳተፍንም ባይ ናቸዉ።

ዛሬ እንዳዲስ ባገረሸዉ ዉጊያ ባለፈዉ ሐምሌ ከሰሜን ሱዳን የተገነጠለችዉ የደቡብ ሱዳን ጦር ሒጂሊጅ የተባለዉን የሰሜን ሱዳን ግዛትና ባካባቢዉ የሚገኘዉን የነዳጅ ጉርጓድ ተቆጣጥሮታል።በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር አሮፕ ዴንግ ኩኦል እንደሚሉት ጦራቸዉ ሒጂሊጅን የተቆጣጠረዉ የሰሜን ሱዳን ጦር ተኩስ ሥለከፈተበት ነዉ።«ትናንት ሐይላቸዉን ከሒጂሊጅ ወደ ደቡብ ሱዳን አንቀሳቅሰዉ ነበር።የደቡብ ሱዳን መከከላከያ ሐይል በወሰደዉ አፀፋ ጥቃት፥ ጥቃቱን አክሽፎ ወደ ሒጅሊጅ መልሷቸዋል።ከሒጅሊጅ ከተማም አባርሯቸዋል።ሥለዚሕ ባሁኑ ሰዓት የደቡብ መከላከያ ሐይል ሒጅሊጅን እየተቆጣጠረ ነዉ።»

የሰሜን ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ራሕማ መሐመድ ኦስማን እንዳስታወቁት ደግሞ የጁባ ጦር የሁለቱን ሐገራት አዋሳኝ ድንበር አልፎ የሰሜን ሱዳንን ሰባ ኪሎ ሜትር ግዛት ወሯል።ሚንስትሩ አክለዉ እንዳሉት ካርቱም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ለአፍሪቃ ሕብረት አቤቱታ አቅርባለች።የካርቱም መንግሥት ጦር ግን የተያዘበትን ግዛት በሐይል እንደሚያስለቅቅ እየዛተ ነዉ።የአፍሪቃ ሕብረት የሱዳኖችን ዉጊያ በጣም አሳሳቢ ብሎታል።

No comments:

Post a Comment