Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, March 31, 2013

ከቤንሻንጉል አማርኛ ተናጋሪ ዜጎችን በግፍ የማፈናቀሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል

-ጥቃቱ ህፃናትና አረጋውያን ላይም እየደረሰ ነው
አማርኛ ተናጋሪውን ከየቦታው የማፈናቀሉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የመረጃ ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንደሚሉት በዚህ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይ ዞን ያሶ ወረዳ 25 ሺህ አማርኛ ተናጋሪዎች እየተደበደቡ በጭነት መኪና ተጭነው ከመኖሪያቸው ተባረዋል፡፡ የአካባቢው የዓይን ምስክሮችም ተጧሪ አረጋዊያንና ህፃናት “ውሃ፣ አምባሻ እያሉ በየመንገዱ ሲለምኑ ያለርህራሄ እየደበደቧቸው ወስደዋቸዋል፡፡” ሲሉ በቅሬታ ያስረዱሉ፡፡

የመንግስትን ዘር ማፅዳት ዘመቻ ማስቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው

ፍኖተ ነጻነት ርዕሰ አንቀጽ

አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የጻፈው ግን የማያነበው፣ አስከብረዋለሁ የሚለው ግን የማያከብረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት በአንቀፅ 32 ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ በህጋዊ መንገድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር የውጪ ዜጋ በነፃነት በመላ ሀገሪቱ የመንቀሳቀስ፣ የሚኖርበትን ቦታ የመምረጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!!

UDJ HeadPic21አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡

ታላላቅ የታሪክ ክህደቶች ከ“ፍኖተ ገድል”

ገብረመድህን አርአያ
ገብረመድህን አርአያ (ተጻፈ ሚያዝያ 6, 2004 ዓ.ም.)

ለአንድ ሰሞን ለአመታት በአሜሪካኗ ግዛት ኦሃዮ ውስጥ በስደት ሲኖር የነበረው የወያኔ ነባር ታጋይ፣ በስለላ የሰለጠነ … እና መሪህ ባኽታ ብስራት አማረ የጻፈው መጽሃፍ በህትመት ወጥቶ ጉድ፣ ጉድ ከተባለለት በኋላ እኔም እንደ ኢትዮጵያዊነቴ እና እንደ ቀድሞ የህወሃት ቀዳሚ ታጋይነቴ መጽሃፉን አግኝቼ ለማንበብ እና የግሌን ግምገማ ለማድረግ መፈለጌ አልቀረም። ዘግይቶም ቢሆን መጽሃፉ በእጄ ገብቶ የማንበብ እድል አገኘሁ። መቼም ጉድ ነው የሚባለው!! ህወሃት እና በዙሪያው የከበቡት ጉዶች የቅጥፈት እና የክህደት ጉድ ማለቂያ የለውም።

ይህ መጽሃፍ በተከታይ እትም ሊታረም የሚችል ግድፈት አይደለም የተሸከመው፤ እንደዚህ በአገጠጠ ውሸት፣ በህወሃታዊ የታሪክ ክህደት፣ በጥላቻ እና በተንኮል የታጨቀ መጽሃፍ አይቼም፣ አንብቤም አላውቅም። ብስራት አማረ ታሪክ ለዚያውም በጣም የቅርብ ጊዜ ታሪክ አንድ ሰው እንዳሻው ስለጻፈው የመጨረሻው እውነት ሆኖ ይቆያል ብሎ ያምናል። ይህ አስተሳሰብ ላዩን ሲያዩት በጣም ገራገር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በጊዜ አስፈላጊው የእርምት እና የማጋለጥ እርምጃ  ካለተወሰደ የኋላ ኋላ ብዙሃን እንደ  እውነተኛ ታሪክ እና ትንታኔ  ዋጋ ሰጥተው ሊያዩት ይችሉ ይሆናል።

Saturday, March 30, 2013

ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?

ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው።

ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” የሚገመግማቸው፣ እነሱም አምነው የሚገመገሙት ታማኝ አድርባይ ስለሆኑ ብቻ ነው።

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም


ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል፡፡ ምንጭ፤ www.goolgule.com
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።

Friday, March 29, 2013

........እኔ የምለው ከክልል ወደ ክልል እየተንቀሳቀሱ ለመስራት እና ለመኖር ፓስ ፖርት እና ቪዛ ማስመታት ያስፈልገናል እንዴ? By ብሩክ ሲሳይ

እንደሚታወቀው ኢህአዴግ የሚባለው ገዢ ቡድን መንበረ ስልጣኑ ላይ ከወጣ ጀምሮ ብዙ አሳዛኝ ነገሮችን በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ ሲፈፅም ቆይቷል አሁንም እየፈፀመ ይገኛል። ከነዚህ አሳዛኝ ነገሮች አንዱ እንደ አንድ ሀገር በአንድነት ለዘመናት ብዙ ርቀት የተጓዘን ህዝብ ወደ ኋላ በመመለስ የዘር እና ጎሳ ልዩነትን በሚያጎላ አካሄድ፤ ቋንቋን እና ዘርን መሰረት ያደረገ የከሸፈ የፌድራሊዝም አወቃቀር ስርዓት በመከተል እንደ ሀገር ብሄራዊ ስሜት እንዳይኖረን የክልል መንግስት የሚባል መዋቅር መፈጠሩ ነው። 

ሲመስለኝ ፌድራሊዝም በራሱ አስፈላጊ የሚሆነው እንደ ሀገር ተበታትነው በተለያየ አገዛዝ የነበሩ አካባቢወች ልዩነታቸውን በማቻቻል ወደ አንድነት መንግስት ለመምጣት ሲያስቡ እንደ መሸጋገሪያ ራስገዝ የሆነ የፌድራል ስርዓት ይመሰርታሉ፤ እነዚህን ራስ ገዝ ክልሎችም በበላይነት የሚመራና የሚቆጣጠር ከሁሉም አካባቢ የሚወከሉ አካላትን ያካተተ ማዕከላዊ መንግስት ይመሰረታል። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ትናንሽ የተለያዩ መንግስታት የነበሩት የአሜሪካ ግዛቶች የፈጠሯት የዛሬዋ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ነች። 

የዘገየው አብዮት (ተመስገን ደሳለኝ)

‹‹አረብ ስፕሪንግ››ን ተከትሎ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖለቲካ ተንታኞች በዘርፈ ብዙ ቅሬታ በተሞላችው ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነገር መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ ደግመው ደጋግመው መተንተናቸው ይታወሳል፡፡ ለድምዳሜያቸው ገፊ ምክንያት አድርገው ከወሰዷቸው ችግሮች ውስጥ ስርዓቱ ለሁለት አስርታት በስልጣን ላይ መቆየቱ፣ አስከፊ ድህነት መስፈኑ፣ የስራ አጥ ቁጥር ማሻቀቡ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ክብር አልባ መሆናቸው፣ የፍትህ እጦት… ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 

ቁጥራቸው የበዛ ምሁራኖች እነዚህ ችግሮች በጊዜ መፍትሄ ካላገኙ አብዮት ወደ ሚያቀጣጥል ‹‹ካምሱር››ነት ለመቀየራቸው የተለያዩ ሀገራትን ታሪክ ጭምር ጠቅሰው በርካታ ፅሁፎችን አስነብበዋል፡፡ የሆነ ሆኖ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ህዝቦች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መነቃቃት ለማደብዘዝ ስርዓቱ ራሱን ለተጋነነ ወጪ መዳረጉ ይነገራል፡፡ በተለይም የደህንነት ተቋሙን፣ መከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊትን ለማጠናከር የሀገር ሃብት ባክኗል፡፡

Monday, March 25, 2013

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው

ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡

Thursday, March 21, 2013

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ


ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዱዋቸውና በመተካካት ረገድ እምብዛም ለውጥ ያልታየባቸው ጉባዔዎች በአብዛኛው ነባር አመራሩን ይዘው ሲያስቀጥሉ መጠነኛ የሆነ እርምጃም ወስደዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ኦህዴድ አቶ አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩን እና ኩማ ደመቅሳን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ሲያሰናብት፤ ብአዴን በበኩሉ የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ብርሃን ኃይሉን፣ደኢህዴን ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋን አሰናብቷል፡፡
ብአዴን በጤና ችግር መደበኛ ስራቸውን ማከናወን የተሳናቸውና ነባር ታጋይ የሆኑትን አቶ ህላዊ ዮሴፍን፣ኦህዴድ ወ/ሮ አስቴር ማሞን በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት እንዲመረጡ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ኦህዴድ የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነሩን አቶ ወርቅነህ ገበየሁን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡