Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, May 6, 2012

በምዕራፍ ብርሃኔ,   Reporter
‹‹የእኔ የሒሳብ ቀመር ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ በዓለማችን ላይ ከ100 ዓመታት በላይ ሲሠራበት የቆየውን የጋውስን የሒሳብ ቀመር ስህተት እንደሆነ ይረጋገጣል ማለት ነው፤›› ያለው የ17 ዓመቱ ወጣት ናኤል ኃይለማርያም ነው:: 

ናኤል የ11 ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር ማንኛውንም ትንሽ ቁጥርን ከማንኛውም ትልቅ ቁጥር ላይ ለመቀነስ አልያም ደግሞ ከማንኛውም ትልቅ ቁጥር ማንኛውንም ትንሽ ቁጥርን ለመቀነስ የሚያስችል የሒሳብ ቀመርን (ፎርሙላን) የፈጠረው:: 

 ነገሩ የተጀመረው እንዲህ ነው:: ናኤል ከስድስተኛ ክፍል ወደ ሰባተኛ ክፍል ሲያልፍ በነበረው የክረምት ወቅት ላይ በዚያን ጊዜ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ታላቅ ወንድሙ የፍሬድሪክ ጋውሰ ቲዮሪን Sn=A1+A2+A3+…+An የሚለውን የሒሳብ ቀመር ተጠቅሞ ከ1 እስከ 100 ያሉትን ቁጥሮች እንዲደምርለት ይጠይቀዋል::

በቀመሩ መሠረት ቁጥሮቹን መደመር የጀመረው ናኤል፣ እስከምሽቱ ድረስ ቢሞክርም ውጤቱን ለማምጣትና መጨረስ ግን አልቻለም ነበር::  ‹‹ከተኛሁ በኋላም የማሰላስለው የድምሩ ውጤት ስንት ይሆናል የሚለውን ነበር::  ውጤቱን ለማምጣት ጓጉቼ ስለነበርና እንቅልፌም እምቢ ስላለኝ ከአልጋዬ ተነሥቼ ቁጥሮቹን መደመር ቀጠልኩ::

በመጨረሻም በመደመርያ ማሽን የታገዘው ጥረቴ ስኬታማ ሆኖ መልሱን ለማወቅ ችያለሁ፤›› ያለው ናኤል፣  የራሱን ቀመሩን ለመፍጠር መንደርደሪያ የሆነውን ምክንያት አስታውሷል:: ከዚያም በኋላ ታዳጊው የራሱን ቀመር መፍጠር እንደሚችል በራስ የመተማመኑ ስሜት አይሎ የራሱን ቀመርን ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለቱን የተያያዘው:: 

ከዚያም ከ157 ዓመታት በላይ ሲሠራበት የቆየው የፍሬድሪክ ጋውስ ቲዮሪ ተቃራኒ የሆነውን ቀመር En=A1-(A2+A3+…+An) እና Tn=An-(An-1+An-2+…+An) የሚለውን ቀመር የፈጠረው:: ናኤል የቀመሮቹን መጠርያ En እና Tn የሚለውን ስያሜ ከእናቱ ኤደንና ከአባቱ የቤት ስም ታታ ከሚለው እንዳወጣው ገልጿል:: ከአንደኛ ክፍል እስካሁን ድረስ በልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤት ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኘው ናኤል ቀመሩን ሠርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ተከታታይ ዓመታት ወስዶበታል:: በናኤል በሁለቱ ቀመሮች ስር ስድስት ቀመሮችንም የሠራ ሲሆን እንደሚባሉም አስረድቷል::

የናኤል ቀመሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎ ካምፓስ በሒሳብ ዲፓርትመንት ለሚገኙ ምሁራን መጋቢት 15 ቀን 2004 ዓ.ም. አቅርቧል:: ቀመሩን ለማየትና ለመገምገም የተሰበሰቡት ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮችም የታዳጊው ቀመር አዲስ እንደሆነ መስክረው ቀመሩ ላይ ምንም ዓይነት ስህተት እንደሌለው ገልጸዋል:: በዕለቱ ከነበሩት ምሁራን መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብና ኮምፒውተር ሳይንስ ፋከልቲ ዲን የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ጉታ አንዱ ናቸው::

ዶ/ር ብርሃኑም ‹‹ናኤል ቀመሩን የሠራበት እያንዳንዱ አካሔድ ትክክልና በመጨረሻ ላይም የሚደርስበት ድምዳሜ ፍጹም ትክክል ነው፤›› ብለዋል:: ዶክተሩ እንዳብራሩት ከሆነ የናኤል ቀመር በከፍተኛ ደረጃ የተሠራ ከመሆኑም በላይ፣ አንድ የቅድመ ምረቃ ለመመርቂያው ሊሠራ የሚችለውን ዓይነት ሳይንሳዊ ጽሑፍ ታዳጊው ጽፏል:: የቀመሩ (ሒሳቡ) ርዕስ፣ ቀመሩን ያስረዳበት መንገድ፣ የቀመሩ ጥልቀት፣ ሎጂካል (ተጠየቃዊ) የሆነው የቀመሩ ፍሰትና በቀመሩ መሠረት ተሠርተው የሚገኙት የመጨረሻዎቹን ውጤቶች ለማምጣት የተጠቀማቸው መንገዶች በጣም ጥሩ እንደሆኑ ዶክተሩ አያይዘው ገልጸዋል::

ዶ/ር ብርሃኑ በተጨማሪም እንዳብራሩት ከሆነ እርሳቸውንም ሆነ ሌሎቹን ምሁራን ይበልጥ ያስደመመው፣ ናኤል የቀመሩን ዝርዝር ሁናቴ ለታዳሚው ሲያቀርብ ከቀመሩ መነሻ ጀምሮ እስከ ድምዳሜው ድረስ አንድም ስህተት በሌለው ሳይንሳዊ በሆነ በጥሩ አገላለጽ ቀመሩን መሥራቱ ነበር:: ‹‹ሒሳብ ከፈሩት የሚሸሽ ከደፈሩትና ከቀረቡት ደግሞ የሚቀርብ ትምህርት ነው፤›› የሚለው ናኤል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተገኝቶ የቀመሩን ፍሰት ለምሁራኑ ባስረዳበት ወቅት የቀመሩ ስሌት ትክክል በመሆኑ ስህተት እንደሌለውና ቀመሩም ፍጹም አዲስ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችሏል::

ናኤል በመጪው ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚካሔደው ዓለም አቀፍ የሒሳብ ምሁራን ስብሰባ ላይ አዲሱን ቀመሩን ያቀርባል:: በዕለቱም ዓለም አቀፍ የሒሳብ ምሁራን የስብሰባው ተሳታፊ ይሆናሉ:: ‹‹የዓለም አቀፍ የሒሳብ ምሁራን ስብሰባን ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በአሜሪካ የሚገኘው ቴምፕል ዩኒቨርሲቲ በጋራ ሆነው ነው:: የናኤል ሥራ በፕሮግራሙ ላይ ቀርቦ ማረጋገጫ ከተሰጠው በኋላ በኤክስፐርቶችና በሒሳብ ምሁራኑ ቀመሩ ይታያል:: 

ከዚያ በኋላ ናኤልም ሆነ ምሁራኑ ቀመሩ ላይ የሚጨምሩትም ይሁን ማስተካከል የሚፈልጉት ነገር ካለ ያ እንዲሆን ይደረጋል:: በመቀጠልም ወደፊት በሚካሔዱ ትልልቅ የሒሳብ ስብሰባዎችና መድረኮች ላይ ቀመሩ እንዲተዋወቅ ይደረጋል:: ይህ ከሆነ በኋላ የቀመሩ ሁኔታ በደንብ ታይቶ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካትቶ ለማስተማርያነት ይሆናል ወይ የሚለው ጉዳይ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል፤›› ሲሉ ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል::

ናኤል የሒሳብ ቀመርን መፍጠር የቻለ ታዳጊ ነው:: ሁሉንም የሒሳብ ፈተናዎቹን ሲሠራ በ15 ደቂቃ ውስጥ ያጠናቅቃል:: ይህ ፍጥነቱ ግን የሒሳብ ውጤቱ መቶ ከመቶ እንዳይሆን ምክንያት ቢሆንበትም ሁልጊዜ ከ80 እና ከ85 በላይ እንደሚያመጣ ተናግሯል:: ናኤል የሒሳብ ቀመርን መፍጠር መቀጠል የሚፈልግ ሲሆን፣ የራሱን ቀመር ‹‹የሒሳቡ ልኡል›› ተብሎ ከሚጠራው ከፍሬድሪክ ጋውስ ጋር የማወዳደር ሞራል ያለው ታዳጊ ነው:: ናኤል ፍጹም ፍላጐቱ በሆኑት ኮምፒውተርና ሶፍትዌር ነክ የሆኑ ሥራዎች ላይ የተለያዩ ፈጠራዎችን በተጨማሪም ለመሥራት አቅዷል::

ሚስቱን በአሲድ አቃጥሎ የገደለውና ደቡብ ሱዳን የተያዘው የሞት ቅጣት ተወሰነበት

በታምሩ ጽጌ, Reporter
ግብረ አበሮቹ ከ16 እስከ 23 ዓመታት ጽኑ እስራት ተቀጡ

አምና ሚያዝያ 30 ቀን 2003 ዓ.ም በልጁ እናት ላይ አንድ ሊትር ሰልፈሪክ አሲድ በመድፋት ለሞት የዳረጋት ግለሰብ፣ ከትናንት በስቲያ በሞት እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ሰጠ፡፡

በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት የሟች የወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ባለቤት የነበረው አቶ ምናለ አቻም፣ በልጁ እናት ላይ አንድ ሊትር ሰልፈሪክ አሲድ በማርከፍከፍ ከተሰወረ ከወራት በኋላ፣ ባለፈው ዓመት ነፃነቷን ባገኘችው ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ውስጥ ተይዞ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ይታወሳል፡፡

ግለሰቡ የፈጸመው የወንጀል ድርጊት በፍርድ ቤት ሲታይ ከቆየ በኋላ፣ ከሳሽ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተበትን ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ሲያረጋግጥ፣ ግለሰቡ የቀረበበትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ባቀረባቸው የመከላከያ ምስክሮችና ሰነዶች ማስተባበል ባለመቻሉ፣ ሚያዝያ 26 ቀን 2004 ዓ.ም ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ከትናንትና በስቲያ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስትን ለመግደል ባለቤቷ ያዘጋጀውን አንድ ሊትር ሰልፈሪክ አሲድ ደብቆ በማቆየትና በመተባበር ጥፋተኛ የተባለው ዘለዓለም ውበት ወይም በቅፅል ስሙ ‹‹ጉቼ ውበት›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በ16 ዓመታት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡ ዘለዓለም የደበቀውን ሰልፈሪክ አሲድ ተቀብሎና ክዳኑን ከፍቶ ለባለቤቷ የሰጠውና በተባባሪነት በሠራው ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው ነበረ ጎሹ ወይም በቅፅል ስሙ ‹‹ቀበሮው›› በመባል የሚታወቀው በ23 ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

ተባባሪዎቹ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ለአምስት ዓመታት ከማንኛውም የሕዝባዊ መብቶቻቸው ታግደዋል፡፡ ሦስቱም ግለሰቦች ማለትም ባለቤቷ ምናለ አቻምና ሁለቱ ተባባሪዎቹ ሚያዝያ 30 ቀን 2003 ዓ.ም የሦስት ሕፃናት እናት የነበረችውን ትዕግስት መኮንን፣ ወደ ቤቷ ልትገባ ትንሽ ሲቀራት በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 19 ሂልሳይድ ትምህርት ቤት አጠገብ፣ ባልየው በዱላ ደብድቦ ከጣላት በኋላ ተባብረው ሰልፈሪክ አሲድ በመላ ሰውነቷ ላይ አርከፍክፈውባት መሰወራቸውን፣ ሆስፒታል ተወስዳ ለሦስት ቀናት ሕክምና ከተደረገላት በኋላ ግንቦታ 2 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ ከዚህ ዓለም ሕይወቷ ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ምጥ ይዟት የነበረች እንስት በማጅራት መቺዎች ሕይወቷ አለፈ

 By Reporter
የበኩር ልጇን ለመገላገል ሰዓታት ቀርተዋት የነበረች የ28 ዓመት ወጣት ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እየተወሰደች ማጅራት መቺዎች ባሏን በመደብደብ ላይ እያሉ ገፍትረዋት በመውደቋ ሕይወቷ ማለፉን ባለቤቷ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡ በምጥ ጭንቅ ውስጥ እያለች ተገፍትራ በመውደቋ ሚያዝያ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ሕይወቷ ስላለፈው ወ/ሮ ምሥራቅ አክመል፣ ባለቤቷ ስለተፈጠረው አጋጣሚና እንዴት ሕይወቷ እንዳለፈ በዝርዝር ተናግሯል፡፡

 የሟች ምሥራቅ አክመል ባለቤት አቶ ታሪኩ ጉዲሳ እንደገለጸው፣ ምሥራቅ ሚያዝያ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ምጥ ይመጣባታል፡፡ የሚኖሩት ላፍቶ ቁጥር ሁለት ኮንዶሚኒየም ቤት በአንዱ ብሎክ ውስጥ ነው፡፡  ቤታቸው ለአስፋልቱ ቅርብ በመሆኑ ታክሲ ይዞ ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ወጥቶ ይቆማል፡፡ ታክሲ ሊያገኝ ባለመቻሉ ተመልሶ ወደ ቤቱ ይገባና ታክሲ እንዳጣ ሲነግራት፣ ምሥራቅ ‹‹እኔን ይዘህ አስፋልት ላይ ብትቆም አዝነው ይወስዱናል›› ስትለው፤ ተያይዘው ወጥተው ደጅ ይቆማሉ፡፡

ትንሽ እንደቆሙ አንድ ላዳ ከጐፋ ወደ ላፍቶ ሲመጣ የተመለከቱት ባልና ሚስት እጃቸውን ሲያውለበልቡ ታክሲው ዝም ብሎ ትንሽ ካለፋቸው በኋላ፣ አንድ ሰው አውርዶ ተመልሶ ይመጣና አጠገባቸው ይቆማል፡፡ ምጥ እንደተያዘችበትና ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው ላንድማርክ ሆስፒታል እንዲያደርሳቸው የተጠየቀው የላዳ ሾፌር፣ አንድ መቶ ብር እንዲከፍሉ ሲጠይቃቸው ይስማሙና እሷ ከፊት እሱ ከኋላ ይሳፈራሉ፡፡

ታሪኩ ከኋላ ሲገባ አንድ ሰው ተቀምጦ ማየቱንና ትንሽ እንደተጓዙ በስካር መንፈስ፣ ‹‹የምከፍለው ይኼንን ያህል ነው›› ሲል ሾፌሩ ደግሞ ‹‹ካወረድኩት ሰው ጋር የተስማማሁት ይኼንን ያህል ነው›› በመባባል ሲነጋገሩ ባልና ሚስት ዝም ብለው ይሰማሉ፡፡ ላዳው ጐፋ ገብርኤል አደባባይ ሲደርስ አደባባዩን በመዞር ወደ ላፍቶ አቅጣጫ የአደባባዩ ጫፍ ላይ ውረዱ ብሎ ባልና ሚስቶቹን በማውረድ ወደ ላፍቶ ይሄዳል፡፡ 

ታሪኩና በምጥ ላይ ያለችውን ምሥራቅን ያጋጠማቸው ሌላ ላዳ ሳይሆን ሁለት ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ማጅራት መቺዎች ነበሩ፡፡ ‹‹ማነህ ምንድነህ›› ሳይሉ በታሪኩ ላይ የቡጢና የእርግጫ ውርጅብኝ ሲያዘንቡበት፣ በምጥ የተያዘችው ምሥራቅ እየለመነች ልትገላገል ስትሞክር፣ ማጅራት መቺዎቹ ከሩቅ ሰው በማየታቸው ወይም ድምፅ በመስማታቸው ይመስላል እሷን በኃይል ገፍትረዋት ይሮጣሉ፡፡ በጉልበተኞች የተገፈተረችው ምሥራቅ በሆዷ መሬት ላይ ትወድቃለች፡፡ ታሪኩም ለብቻው ወድቆ ነበርና ምሥራቅ በድንጋጤ ውስጥ ሆና በመነሳት ወደ ባሏ ተጠግታ ‹‹ተረፍክ›› ካለች በኋላ ተዝለፍልፋ መውደቋን ባለቤቷ በዝርዝር ተናግሯል፡፡

በምጥ ጭንቅ ላይ የነበረችው ምሥራቅ ተዝለፍልፋ ስትወድቅ እሷን አቅፎ የድረሱልኝ ጩኸት ቢያሰማም ምንም ዕርዳታ አለማግኘቱን የገለጸው ባለቤቷ፣ አንድ ታክሲ ሲመጣለት ታቅፎ በማስገባት ላንድማርክ ሆስፒታል ቢያደርሳትም፣ ከዶክተሮቹ የተነገረው መርዶ ሕይወቷ ያለፈው በክንዱ ላይ መሆኑን በማንባት ገልጿል፡፡

ታሪኩና ምሥራቅ የተጋቡት ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. መሆኑንና አብረው መኖር ከጀመሩ ገና ዘጠነኛ ወራቸው እንደሆነ ተናግሮ፣ ‹‹እኔና እሷን ጨምሮ የእሷና የእኔ ቤተሰቦች፣ ጓደኞቻችን፣ የሥራ ባልደረቦቻችን ጭምር የልጃችንን መወለድ ስንጠባበቅ ቆይተን፣ በገዛ አገራችን ውስጥ ይኼ ወንጀል ተፈጸመብን፤ ላልሰሙት ወገኖቻችን ምን ብዬ ልንገራቸው?›› በማለት መሪር ሐዘኑን ገልጿል፡፡

ምሥራቅ የተወለደችውና ከ27 ዓመታት በላይ ዕድሜዋን ያሳለፈችው ሐረር ከተማ ውስጥ መሆኑን የገለጸው ባለቤቷ፣ አስከሬኗ ምኒልክ ሆስፒታል ከተመረመረ በኋላ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. ሐረር ከተማ ውስጥ ሥርዓተ ቀብሯ መፈጸሙን ገልጿል፡፡

በአስጐብኝነት ሥራ ላይ የተሰማራ መሆኑን የገለጸው ታሪኩ፣ የባለቤቱን ማርገዝ ለውጭ ዜጐች ጭምር ሳይቀር መናገሩን ጠቅሶ፣ ‹‹የሃይማኖት አገር፣ የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት በምትባለው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለቤቴን ማጅራት መቺዎች ገደሉብኝ ብል ምን ይሉኛል?›› በማለት በምሬት ተናግሯል፡፡ ‹‹ክፉ ናቸው፣ ሰው በላ ናቸው፣ በማለት ከሚታወቁት አንዳንድ አገሮች የበለጠ ክፉዎች ነን፤ ምናልባት እሷን ትተው የፈለጉትን በመውሰድ ቢለቁን? በወቅቱም የለመንናቸው ይኼንን ነበር፤›› ሲልም በምሬት አስረድቷል፡፡

ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መኖሩን የገለጸው ታሪኩ በሲቃ ውስጥ ያለ ድምፅ ቢሆንም፣ የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ ማንም እንዳልደረሰለት፣ በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ማንም ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለው እንደሚሰማው ተናግሯል፡፡ አንድ ሰው ሲሰረቅ ወይም ሲደበደብ የሚያይ ሰው እንዳላየ የሚሆነው፣ ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ ከቀናት በኋላ ከእስር ሲለቀቁ የሚያደርሱበትን ድብደባ ስለሚፈራ መሆኑን፣ እነሱ ሲደበደቡ በርቀት ሆኖ ይከታተል የነበረ አንድ ግለሰብ ለፖሊስ ከሰጠው ቃል ሊገነዘብ መቻሉን ታሪኩ ይናገራል፡፡

ግለሰቡ በርቀት ሁኔታውን በሙሉ ሲከታተል ስለነበር ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ሁለቱም ግለሰቦች ቢያዙም፣ ሆን ብሎና ተሻርኮ እነሱ ጋ ያደረሳቸው ባለላዳ እንዳልተያዘ ገልጿል፡፡ መንግሥት ለእሱ (ለታሪኩ) ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ፍትሕ በወንጀለኞቹ ላይ እንዲሰጥም ጠይቋል፡፡

ምጥ ተይዛ ወደ ሆስፒታል በመሄድ ላይ ሳለች ሕይወቷ ስላለፈው ወ/ሮ ምሥራቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የነፍስ ግድያና ወንጀል ምርመራ ዲቪዚዮን ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ‹‹ድርጊቱ አሳዛኝ ነው›› ብሎ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች ተይዘው በምርመራ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

Saturday, May 5, 2012

Norway To Asylum Seekers: Go Home

By Courtney Brooks, Amina Umarova
Magomed was recently rounded up in the middle of the night and deported from Norway without warning.

The 40-year-old Chechen asylum seeker says he was not even informed that his request had been rejected after seven years living in the country. By The Numbers: Norway's Asylum Seekers 

"They brought us to Moscow and left us completely alone," he says. "Many of us did not have proper documents and therefore they kept us at the border for a long time. [The Norwegians] told us that their duty was to hand us over to the Russian authorities."

Magomed, who declined to give his full name out of fears for his safety, is now living in Chechnya with his parents. He has been left without a job or any money and doesn't know who to turn to for help. And his is far from an isolated case.

Asylum Numbers Drop
Members of 50 other families living in Norway were deported the same night he was. The number of asylum seekers who have been deported or who have had their applications denied has increased dramatically in Norway as the result of the government's push to drive out illegal immigrants. The rise came even as the number of asylum seekers dropped in 2010, putting the spotlight on the toughening of an asylum process once seen as one of the more welcoming in Europe.

A look at the numbers provided by the Norwegian Directorate of Immigration for January 2009 through February 2011 shows that asylum seekers from Muslim-majority states or regions are disproportionally affected, with citizens of Afghanistan, Iraq, and the North Caucasus regions of Russia accounting for a large percentage of the rejected claims. Considering the instability or authoritarian regimes seen in many of the asylum seekers' home regions or states, fears for their well-being are being raised.

Norway has noted that asylum seekers are entitled to protection if they are in danger of being killed, tortured, or "exposed to other forms of grave abuse" upon being returned to their home country.
European Union Human Rights Commissioner Thomas Hammarberg has denounced Norway specifically for sending Iraqi immigrants back to five provinces in Iraq -- including Baghdad -- that the United Nations Human Rights Commission (UNHCR) considers too unsafe for the return of asylum seekers. 
Irfan Qaiser, a policy adviser at the refugee advocacy group Norwegian People's Aid, says the general attitude toward immigrants, and Muslims in particular, has deteriorated in recent years. "I think in general the tendency [in Europe] has been -- I mean, we see that here in Norway as well -- that the political debate has definitely been going towards more control, more restrictions, and also linked into general integration debates," he says.

"You know, the debate we see in Europe now about the death of multiculturalism, etc., etc. -- that people need to follow, we need to have clear demands on people who come here, and we need to know what they're doing, what they're up to, even into a debate where they have less rights than the rest of the population."
Debate Erupts
In recent years, debate over asylum laws has erupted across the Nordic countries. Incidents linked to the 2005 cartoon controversy in Denmark -- including the burning of Danish embassies in Syria, Lebanon, and Iran, and a suicide blast carried out by an Iraqi-born bomber in Stockholm in December -- have caused antipathy toward Muslim asylum seekers.

Last year, 1,444 asylum seekers and illegal immigrants returned voluntarily to their home countries with support from the Norwegian authorities, a 30 percent increase over the previous year, according to the Norwegian Directorate of Immigration's website. One in three was Iraqi.

But there has also been a significant rise in the number of asylum seekers, like Magomed, who are being forcibly deported from the country. Seventy-one Iraqis were deported in the first two months of this year alone, higher than for all of 2009, according to data from the Norwegian Police Immigration Service.

The number of asylum seekers forcibly sent to Russia, a large proportion of which are from North Caucasus republics like Chechnya and North Ossetia, has skyrocketed. There were 102 people deported to Russia in the first two months of this year, equal to the entirety of 2010. 
The most prominent was 25-year-old Madina Salamova, better known by her pseudonym Maria Amelie. She wrote a book about her experience fleeing from North Ossetia to Norway as a child. In 2010, Salamova was named "Norwegian of the Year" by a weekly news magazine, and her deportation prompted protests across the country. EU rights commissioner Hammarberg tells RFE/RL that, considering Chechnya's current political situation, only voluntary returns should be made to that republic.

Dangers At Home
There is evidence that other returnees also face danger after being sent home. According to the NGO Iran Human Rights, a 19-year-old Iranian Kurd named Rahim Rostami, who was denied asylum by Norwegian authorities and deported in February, now finds himself in prison in Iran. 
The group reports that he is in danger of torture, ill treatment, or death at Tehran's notorious Evin prison. Data from the Norwegian Directorate of Immigration shows that between January 2009 and February 28 of this year, 8,289 people from Afghanistan, Iraq, and Russia applied for asylum in Norway.

During the same period of time, 6,111 asylum seekers from these countries had their applications rejected and were left with either appealing the decision or returning to their country of origin within three weeks. Many more were found to be applying for asylum after having their applications rejected in another country in the Schengen area and were returned to be dealt with by the country originally responsible for their application. Last year, appeals were upheld in 6.8 percent of cases.

According to the UNHCR, there was a 42 percent decrease in the number of asylum claims in Norway in 2010 compared to 2009. The number of claims rejected rose, however -- from 6,196 in 2009 to 7,673 in 2010. A spokesperson for the Directorate of Norwegian Immigration, Kirsten Myhre, says the number of asylum seekers has decreased because the country has been so strict over the last two years. She explained how the department weeds out those it doesn't think are in need of protection.

"They are very often not credible," she says. "They are interviewed for more or less one day, and often they don't give information...that they are persecuted at all. They say they have been to prison and released after one hour. Well, if the government really wants them they would have been watched more."

Preserving The System
Hanne Mathisen, a spokeswoman for the UNHCR's office for Baltic and Nordic countries, says the Norwegian government has stepped up its efforts to remove illegal immigrants in order to ensure the system is not abused. "There is a renewed emphasis on the part of the Norwegian government to ensure that persons that are rejected in the asylum procedure return voluntarily, and if they don't, then that return will happen by force," she says.

"The argument they're making is that it is necessary in order to deter persons that abuse the asylum system, that are actually not in need of international protection. It's also important in order to uphold the integrity of and support for the asylum system."

Qaiser of Norwegian People's Aid says there have not been many cases of the Norwegian immigration procedures breaking international conventions -- with the notable exception of a report showing that asylum seekers in some detention centers were woken up every half hour to "prevent them from committing suicide," a form of sleep deprivation Qaiser says is internationally acknowledged as torture.

Rather, immigration authorities, he says, push to the outer limits of what is considered acceptable by international standards. The lack of transparency in the system is what is most worrying to human rights activists.
"The whole deportation regime is so closed, it's hard to know what goes on, what kind of procedures," he says. "But from time to time we see that police go in the middle of the night picking up families, placing families and children, sending them to these deportation centers. And...we have gotten reports that what goes on in those deportation centers from time to time may be defined as harsh and degrading treatment."

Asylum seekers, meanwhile, just want a place to call home. Letchi, a Chechen who was a neighbor of Magomed, says his brother was part of the group deported to Russia. "If they send people back to Chechnya, then they should not keep them for such a long time here [in Norway]," he says. "While they are living here, their children are attending schools. And what should they do back at home [in Chechnya]? Study all over again? The children are suffering. They are neither here nor there.

"My brother and his family were sent back in that way. My brother and Magomed were waiting for the court's decision regarding their status. But they came to him in the night, handcuffed them, and sent them out despite their lawyers' protests. The police say they just follow orders."

Alisher Sidikov and Zamira Eshanova of RFE/RL's Uzbek Service and Merkhat Sharipzhanov of RFE/RL's Central Newsroom contributed to this report

Source: http://www.rferl.org/content/norway_asylum_seekers_iraq_chechnya_afghanistan/3545141.html

Unlawful Imprisonment In Ethiopia: Intimidated, Tortured And Detained — OpEd

By Graham Peebles | Eurasia Review

Arrested, jailed and beaten, tortured and imprisoned, this is the recipe for justice that the Ethiopian government serves up to dissenting voices. Men and women peacefully exercising their democratic right, demanding their human rights, crying out for their moral rights.

The victimised are not only those living within Ethiopia who attempt to offer an alternative to the current dictatorship, who form and organise political opposition to the Meles regime, but journalists inside Ethiopia and abroad, who dare to speak out in criticism of the governments criminality, human rights violations and policies of indifference.

Amnesty International in its damning report of the Ethiopian government, Dismantling Dissent in Ethiopia (DDE);1 state that from March to November 2011 “at least 108 opposition party members and six journalists have been arrested for alleged involvement with various proscribed terrorist groups.” By November they were all charged with crimes under the internationally criticised Anti Terrorist Proclamation. In addition, Amnesty continues, “six journalists two opposition party members and one human rights defender, all living in exile, were charged in absentia.”


The ‘T’ word as former Secretary General of the UN Kofi Annan, called terrorism, is the umbrella term used by the Ethiopian government (amongst others) to justify the unjust, the dishonest and the criminal. If there is a terrorist organisation flourishing in Ethiopia, committing crimes against humanity and violating the human rights of the people it is State terrorism delivered by the EPRDF government, under the leadership of Prime Minister Meles Zenawi, as this UN definition of terrorism makes clear.

“Criminal acts intended or calculated to provoke a state of terror in the general public, a group of persons or particular persons for political purposes are in any circumstance unjustifiable.”2 Fear of the government, fear of reprisal, of violence and [false] imprisonment casts a deep shadow across the people of Ethiopia, whose human rights are being ignored by the Meles regime, that seized power twenty years ago and has brutalised and systematically restricted the peoples freedom and human rights ever since.

Lawless lawmakers
In 2009 the Ethiopian government passed legislation on the highly controversial Anti Terrorism Proclamation. Human Rights Watch (HRW)3 that year looked closely at what was then the proposed law and amongst other recommendations held high within their fury and despair, said, “if implemented this law could provide the Ethiopian government with a potent instrument to crack down on political dissent, including peaceful political demonstrations and public criticisms of government policy” and “It would permit long-term imprisonment and even the death penalty for “crimes” that bear no resemblance, under any credible definition, to terrorism.

 It would in certain cases deprive defendants of the right to be presumed innocent, and of protections against use of evidence obtained through torture.” Needles to say, the law was passed almost entirely as drafted, duly implemented and has since been used solely to silence dissent. Amnesty in its report found “the prolonged series of arrests and prosecutions indicates a systematic use of the law and the pretext of counter-terrorism by the Ethiopian government to silence people who criticise or question their actions and policies, especially opposition politicians and the independent media.”

It is the utilisation and enforcement of this unlawful law that is enabling the Ethiopian government to quash opposition and free speech within the country and intimidate those voices for fairness, justice and common sense abroad. The legislation allows the government to ban free association and to arrest and imprison anyone who has the courage to speak out against the government and their many human rights violations. The police, who were already commonly acting outside of the law, with little or no knowledge of human rights, were given new and unlawful powers.

HRW in its analysis states, “The draft Proclamation grants the police the power to make arrests without a warrant, so long as the officer “reasonably suspects” that the person is committing or has committed a terrorist act. The Ethiopian constitution requires that a person taken into custody must be brought before a court within 48 hours and informed of the reasons for their arrest-a protection that is already systematically violated.”

This constitutional requirement as with many articles of decency and good intention is dutifully ignored. Arrested under the Anti Terrorist Proclamation individuals are held in confinement for weeks, sometimes months without charge and denied legal support. Even before this draconian legislation was enforced HRW states “Ethiopian police routinely detain people without charge for months, and sometimes ignore judicial orders for release.”
 

 Five from many
In January five more innocent people were convicted in the Ethiopian Federal High Court, of conspiracy to commit terrorist acts, and money laundering. Evidence against the three journalists an opposition leader and a woman, Hirut Kifle Woldeyesus, was made up primarily of online criticism of the government and plans to stage peaceful political protest. None of which constitute acts of terrorism. This is common as Amnesty found in the 114 cases they investigated in their detailed report, “much of the evidence against those charged involves items that do not appear to amount to terrorism or criminal wrongdoing. Rather many items of evidence cited appear to be illustrations of individuals exercising their right to freedom of expression, acting peacefully and legitimately.”

Two of the journalists tried in January were sentenced to 14 years imprisonment while Elias Kifle (tried in absentia), editor of the web-based journal Ethiopian Review, received his second life sentence [emphasis mine]. These cases are simply the most recent in a long line of miscarriages of ‘justice’, where the outlaw government has exercised an abuse of power and in the name of justice imprisoned the innocent. A further 24 journalists and opposition party members are awaiting trial, many of whom could face the death penalty, for trumped up charges which amount to nothing more than journalists exercising their constitutional and moral right to freedom of speech.

The UN Special Rapporteur on human rights defenders, Margaret Sekaggya stated in a meeting of UN human rights investigators in February “journalists, bloggers and others advocating for increased respect for human rights should not be subject to pressure for the mere fact that their views are not in alignment with those of the Government.”4 Indeed. Journalists must be free to speak out against the government, to criticise policies of persecution, to highlight the suffering of the people and to draw attention to the multiple human rights abuses taking place within Ethiopia.

UN Special Rapporteur on freedom of expression, Frank La Rue, “Journalists play a crucial role in promoting accountability of public officials by investigating and informing the public about human rights violations, they should not face criminal proceedings for carrying out their legitimate work, let alone be severely punished.” However all those speaking out in anguish and rage at the EPRDF’s criminality and repression are subject not simply to ‘pressure’, or ‘criminal proceedings’, but violent arrest, torture and false imprisonment, or indeed death.

Free the innocent
These five innocent men and women, who were mistreated in custody, falsely imprisoned and like others, including the celebrated writer Eskinder Nega (imprisoned for life in September for writing an on-line blog), denied their liberty, must be released immediately and an independent enquiry instigated to investigate their cases, their treatment whilst in jail and their hollow convictions. During their three-month imprisonment at the Maikelawi detention center before the trial and in violation of Ethiopian and international law, the defendants were denied access to legal counsel and family members, and claim they were beaten and tortured.

 This is the experience of a great many whilst held in Maikelawi, Amnesty reveals in its report, “many of the [114] detainees were forced to sign confessions and to acknowledge ownership or association by signing items of seemingly incriminating evidence.” The Ethiopian courts have not investigated any of these claims, they are it seems nothing more than servants of the Government, and are as HRW states “complicit in this political witch hunt.” This collusion of the courts contravenes the Ethiopian constitution that states in Article 78/1.

 “An independent judiciary is established by this Constitution. Article 79/1. “Judicial Powers, both at Federal and State levels, are vested in the courts,” furthermore, 3. “Judges shall exercise their functions in full independence and shall be directed solely by the law.” The UN Special Rapporteur on the independence of judges and lawyers, Gabriela Knaul “deplored the reported failure to ensure the defendants’ right to a fair trial.” Reports the UN News Centre.

The Ethiopian government cannot be believed or trusted; the international bodies supporting the country should impose independent observers of the judicial system. Amnesty International in its report calls “on the representatives of the international community in Addis Ababa to take up the role of monitoring trials.” This would be an important initial act in placing the EPRDF under international scrutiny and accountability. It is time the international community acting through the UN undertook its responsibility and role as advocate for justice, self-determination, “the suppression of acts of aggression” (article 1) and freedom for the people of the world, in accordance with its charter.

A blind eye to torture
In addition to the suppression of free speech, the use of the death penalty and withdrawing the legal right of presumption of innocence, torture is allowed under the Anti Terrorism Proclamation and information gathered whilst under such duress is admissible in court. HRW again, “The draft Proclamation deems confessions admissible without a restriction on the use of statements made under torture”. This is illegal under international law, The Convention against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment does not allow the use of any statements made in a court of law, that where elicited under torture. The use of such information is also prohibited under the Ethiopian Constitution.

Article 19 states, “Persons arrested shall not be compelled to make confessions or admissions which could be used in evidence against them. Any evidence obtained under coercion shall not be admissible.” The much-trumpeted constitution in colours green red and yellow, no doubt framed and hung neatly upon a wall of indifference and conceit, unenforced; it means little or nothing to the people and even less to the EPRDF who ignore its charter.

Known unknowables
It is an acknowledged fact within the corridors of the UN and Ethiopia’s donor countries that human rights abuses are occurring daily within the country under the increasingly paranoid gaze of Prime Minister Meles and his ministerial menagerie. How do we as a world community, responsible and alert to the needs of our brothers and sisters, respond to such men, to such injustice and tyranny? Fight fire with fire many would advocate and in the face of such cruelty many of us would perhaps gladly fuel a furnace, however as Mahatma Ghandi said “I cannot teach you violence, as I do not myself believe in it.

 I can teach you not to bow your heads before anyone even at the cost of your life.” To be silent in the sight of injustice and persecution is to allow tyrants like Meles to maintain their stranglehold over the innocent. It is time intense political pressure from those providing and delivering the much-needed financial and developmental aid, was applied to put an end to the current regimes human rights violations and abuse of the people, including freezing of personal assets and targeted sanctions.

The British government give £315 million a year to Ethiopia, a spokesperson from The Department for International Development (DFID) told the Guardian (3/02/2012) “The prime minister, the foreign secretary and the secretary of state for international development have all raised concerns with Prime Minister Meles over the recent arrests of opposition leaders and journalists.”5 ‘Concern’ is all well and good, but all too easy for the arrogant to shrug off, outrage and horror a more apt response from Westminster and more in keeping with the offences being committed. Criticism alone however will not bring change within the abysmal regime and justice to the long-suffering people.

Repeal and release
Prime Minister Meles Zenawi presides over a brutal manipulative dictatorship that restricts all freedom of expression, freedom of association and freedom of the media in Ethiopia. Peaceful dissent is met with violence and false imprisonment. Intimidation and fear are the key tools in such repression, this must end and we the international community must ensure it is so. The Anti terrorist Proclamation is an unjust piece of legislation designed and implemented by a corrupt and violent regime who are in breech of international law and there own constitution. It must be repealed immediately, the many innocent good men and women falsely imprisoned released and those supporting Ethiopia through development aid should insist on the implementation of these legitimate and morally right demands. Sit not in silent appeasement, but raise your bowed heads and act.
Notes:
1. http://www.amnestyusa.org/research/reports/ethiopia-dismantling-dissent-intensified-crackdown-on-free-speech-in-ethiopia
2. 1994 United Nations Declaration on Measures to Eliminate International Terrorism annex to UN General Assembly resolution 49/60 ,”Measures to Eliminate International Terrorism”, of December 9, 1994, UN Doc. A/Res/60/49
3. Human Rights Watch Analysis of Ethiopias Draft Anti-Terrorist Law. http://www.hrw.org/news/2009/06/30/analysis-ethiopia-s-draft-anti-terrorism-law
4. http://www.un.org/apps/news/story.asp?NewsID=41112&Cr=journalist&Cr1
5. http://www.guardian.co.uk/global-development/poverty-matters/2012/feb/03/ethiopia-human-rights-questions?INTCMP=SRCH
About the author:
Graham Peebles is Director of The Create Trust, a UK registered charity, supporting fundamental social change and the human rights of individuals in acute need. He may be reached at graham@thecreatetrust.org

Friday, May 4, 2012

በአቶ መለስ መንግስትና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኢሳት ዜና:-
የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤ “በሀሰት ፕሮፓገጋንዳ የመብት ጥያቄዎቻችን አይዳፈኑም”  በሚል ርዕስ ባለ 15 ገጽ መግለጫ በበተነበት በትናንትናው ዕለት፤ መንግስት  በፊናው የማስጠንቀቂያ እና የማስፈራሪያ መግለጫ አውጥቷል።

 የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ ረዥም መግለጫ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ   በአብዛኛው የሙስሊም ህብረተሰብ ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና ተቃውሞ፤ በምርጫ 97 ወቅት ተከስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር አመሳስሎታል።

 “መንግስት  ለእስልምና እምነትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ካለው አክብሮት በመነሳት  እያሳዬ ያለው ሰፊ ትዕግስት፤ የተቃውሞው አስተባባሪ የሆነው  ህገ ወጥ ሀይል  ከፍርሀት እየተመለከተው  ነው” ሲልም- የአቶ መለስ መንግስት አለመፍራቱን ጠቅሷል።

 እንደ መንግስት መግለጫ፤ ላለፉት 11 ሳምንታት በ አወሊያ እና በአንዋር መስጊድ  እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ   የብዙሀኑ ሙስሊም ጥያቄ ሳይሆን፤ህግና ስርዓትን አክብረው ለመሄድ ዝግጁነት በሌላቸው ሀይሎች  የሚመራ ነው።

 “ እነዚህ ወገኖች  መንግስትም ሆነ የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም የየራሳቸውን ምላሽ እንዳልሰጧቸው በማስመሰል ሰፊ አፍራሽ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄዱ ከመሆኑም በላይ፤ በ1997 ሀገሪቱን ለብጥበጥ ዳርገው ከፍ ያለ ጉዳት ካደረሱትና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተመደቡ ሀይሎች የጥፋት እንቅስቃሴ ጋር በግላጭ ተመጋጋቢ የሆነ ዘመቻም እያካሄዱ ነው” ሲልም ‘የሀይማኖታችን ይከበር!’ ጥያቄ ባነሱ ሙስሊሞች ላይ ፖለቲካዊ ክስ አሰምቷል።

መግለጫው አያይዞም፦“መንግስት ያሳየውን ትእግስት ከድክመት በመቁጠር ፦” መንግስት ፀረ ህገ መንግሰት ሆኗል-ስለዚህ በህገ መንግስቱ የተጎናፀፍናቸውን መብቶች ሊነጥቀን ተነስቷል በማለት እየተቀሰቀሰ ነው” ብሏል።

 እነዚህ ወገኖች ፖል ቶክና ፌስቡክን የመሳሰሉ ዘመናዊ ሚዲያዎችን ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ በማዋል ግርግርና ሁከት እንዲስፋፋ ከሚሹ በሀገር ውስጥ በሚነገሩ ቋንቋዎች ከሚተላለፉ የውጭ ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት በሀገሪቱ መንግስት ላይ የሚያካሂዱት የማጥላላት ዘመቻ መረን የለለቀበበት ደረጃ ደርሷል ሲልም- የፌዴራል ጉዳዮች መግለጫ አብራርቷል።

 በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ የተደነገገ ቢሆንም፤ አቶ መለስና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአህባሽን አስተምህሮ እንዲከተሉ፤ እንዲሁም ባልመረጧቸውና አይወክሉንም ባሏቸው የመጂሊስ አመራሮች እንዲመሩ ግፊት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

 የተቃውሞው መንስኤም ሆነ እስካሁን ድረስ ህዝበ-ሙስሊሙ በሚያደርጋቸው ተቃውሞዎች እያቀረባቸው ያሉት ጥያቄዎችም በዋነኝነት ከነዚሁ ሁለት ነጥቦች ጋር የተያያዘ ነው- ያልመረጥነው የመጂሊስ አመራር ይነሳልን! መንግስት የአህባሽን አስተምህሮ በግዳጅ ህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለመጫን ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ያቁም!” የሚሉ።

 የህዝበ-ሙስሊሙ ጥያቄዎች  በሀይማኖታዊ መብት መከበር ዙሪያ ላይ ያነጣጠሩ ከመሆናቸውም በላይ እስከዛሬ ድረስ በመስጂዳቸው ተወስነው ባሰሙት ተቃውሞ  በተደጋጋሚ፦”መንግስት ድምፃችንን ይስማ!” እያሉ ሲጠይቁ መደመጣቸው ይታወቃል።

 የአቶ መለስ መንግስት ፤አንድ ጊዜ ከአክራሪዎችና ከአሸባሪዎች፤ ሌላ ጊዜ ከተቃዋሚ ሀይሎችና “ኪራይ ሰብሳቢዎች” ከሚላቸው ወገኖች ጋር እያገናኘ ፖለቲካዊ ምስል እየሰጠው ያለው ፤ይህን “የሀይማኖታዊ መብት ይከበር!” ጥያቄ ነው። ከዚህም አልፎ በአርሲ-አሰሳ ከተማ በመስጊዳቸው ተወስነው የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተው ሰባት መግደላቸው እና በርካቶችን ማቁሰላቸው ይታወሳል።

 ግድያውን ተከትሎ  ትናንት የፌዴራል ጉዳዮች ያወጣው መግለጫ፤መንግስት መጠነ ሰፊ የሀይል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን የሚያመለክት ነው።  የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ ደግሞ፦” በሀሰት ክስና ፕሮፓጋንዳ የሙስሊሙን ጥያቄ አዳፍናለሁ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ  መሆኑን ነው ያሰመረበት።

 “ እውነትን እስከያዝን ድረስ፤በሀሰት ተወንጅለን እንታሰራለን ብለን አንፈራም! እንሞታታለን እንጂ ከመብት ጥያቄያችን ወደ ሁዋላ አናፈገፍግም” ነው  እያሉ  ያሉት ብዙሀኑ ሙስሊሞች።
 ለዚህም ይመስላል በ አሰሳ ሰባት ሙስሊሞች  በተገደሉና ሳምንት እና መንግስት  የማስጠንቀቂያ መግለጫ ባወጣ ማግስት  በዋለው በዛሬው የጁምአ ጸሎት እንደ ወትሮው ሁሉ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች  ጠንካራ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

 ለመንግስት መግለጫ ቀጥተኛ ምላሽ በሚመስል መልኩ በ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአንዋር መስኪድ ተገኝተው በአርሲ አሳሳ ከተማ የተገደሉት ሰዎች አሸባሪዎች አለመሆናቸውን እና የመጅሊስ አመራሮችም ከስልጣን ወርደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። ድርጊቱን በስፍራው ተገኝቶ በፊልም የቀረጸው የኢሳት ዘጋቢ እንዳለው በዛሬው እለት የነበረው ተቃውሞ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መንግስት ላወጣው መግለጫ ቁብ እንዳልሰጠው የሚያመለክት ነው።

 ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎፋ አካባቢ በሚገኘው ጀሙ መስጊድ ሌሊቱን ከፍተኛ የሆነ ተኩስ እንደነበር፣ በአካባቢው የሚገኙ የሙስሊም መሪዎችን ለመያዝ ጥረት መደረጉን ለማወቅ ተችሎአል። በሼክ ኮጀሌ መስጊድ ደግሞ 10 ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። አዎልያ ኮሌጅም ዛሬ ተዘግቶ መዋሉን መረጃዎች ደርሰውናል። መረጃዎቹን ከመንግስት በኩል ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። 

የሁለቱም ሀይማኖት ተከታዮች ከመንግስት እኩይ ሴራ እንዲታቀቡ ጥምረት አሳሰበ

ኢሳት ዜና:-
ጥምረት ለነጻነት፡ ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ  ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው መለስ ዜናዊ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ክብደት ስጥቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በማንቋሸሽና በማናናቅ በአለም ከሚታየው አክራሪ ሂደት ጋር በማገናኘት የምእራቡን አለም ቀልብ ለመሳብና ለዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ ሊጠቀምብትም  ላይ ታች እያለ ነው።

ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ሲሰራበት የነበረው ህዝብን በዘር የመከፋፈልና የኢትዮጵያን አንድነት የማናጋት ሴራው እየከሰመ ስለመጣበት ህዝቡን በሃይማኖት ቅራኔ ውስጥ በመዝፈቅ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም እየተፍጨረጨረና እየማሰነ ይገኛል ያለው ጥምረት፣  በቅርቡም የዘረኛው ስርአት መሪ መለስ ዜናዊ ሃይማኖትን በሚመለከት ለአሻንጉሊት ፓርላማዉ ያቀረበው ሀተታ እጅግ አደገኛ ነው ብሎአል።

ጽንፈኝነት በእስላሙም ሆነ በክስርስትያኑ መካከል እየታየ ነው በማለትና በእንጭጩ መቅጨት በሚል ዘይቤ በሰላም አብረው በመኖር የሚታወቁትን የክርስቲያንና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ለማጋጨትና በዚህም ሳቢያ የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለመደምሰስ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ከቅርብ ቀናት በፊት በአርሲ በእስልምና ተከታይ ኦሮሞ ወግኖቻችን ላይ የወሰደው የጭፍጨፋ እርምጃ ይህን የሚያረጋግጥ ነው ሲል ጥምረቱ አክሏል።

የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በሁለቱም ዋና ዋና ላይ ሃይማኖች ላይ በጠላትነት የተነሳ መሆኑን የቅርብ ሳምንታት ተግባሩ ጉልህ ማስረጃ ስለሆነ የሁለቱም ሃይማኖቶች ተከታዮች ይህን እኩይ ሴራ ተገንዝበው የወያኔ ተንኮል መሳሪያ እንዳይሆኑ ጥምረት በአጽኖት ያሳስባል ብሎአል።

የሁሉም ጠላት የወያኔ ዘረኛ ስርዓት ስለሆነ ይህን ግፈኛና ከፋፋይ ስርአት ከስር መሰረቱ ለመፈንቀል በህብረት መታገል ከሁሉም ኢትዮጵያዊ  የሚጠበቅና ዘለቄታዊ መፍትሄ የሚሻ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ያለው ጥምረት ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጳያዊ ዜጋ ለሀገር አንድነትና ለህዝብ መብቶች መከበር እንዲሁም ለነጻነትና ለፍትህ ከዳር እስከ ዳር እንዲነሳ ጠይቋል።

Reeyot honored with 2012 Courage in Journalism and Lifetime Achievement Award

Reeyot Alemu, 31, an Ethiopian columnist currently imprisoned on charges of terrorism after writing critiques of her country’s government; Asmaa al-Ghoul, 30, a Palestinian blogger and freelance writer who has received death threats for her commentary on the culture and politics of Gaza; Khadija Ismayilova, 35, a radio reporter from Azerbaijan who was blackmailed and threatened after her investigation into charges of malfeasance against members of the Azerbaijani president’s family.  These are the International Women’s Media Foundation’s 2012 Courage in Journalism Award winners. “I am humbled to work in the same profession as these heroic women,” said Katty Kay, co-chair of the IWMF.  “It is my honor to be involved with the IWMF as it recognizes their dedication and bravery.  It is journalists like Reeyot, Asmaa and Khadija who set an example for all of us.” 

The IWMF’s 2012 Lifetime Achievement Award is presented to Zubeida Mustafa, 70, a Pakistani journalist who has worked for three decades at Dawn, one her country’s oldest and most widely circulated English-language newspapers.

Theodore Boutrous, Jr., IWMF co-chair, said “A free and independent press is vital to freedom and liberty. The IWMF believes that no press is truly fee if women do not share an equal voice.   As the first woman to work at Dawn, Zubeida blazed a trail for women journalists in Pakistan, changing hiring policies and mentoring young women.  She showed that women journalists can cover serious topics such as healthcare and economic inequality.”  

The 2012 awards will be presented during ceremonies in New York on October 24 and in Los Angeles on October 29. “The IWMF is grateful to the Bank of America, National Presenting Sponsor of the Courage in Journalism Awards for the seventh year and steadfast supporter of heroic women journalists around the world,” said Elisa Lees Munoz, Acting Executive Director of the IWMF.

About the IWMF

Founded in 1990, the International Women’s Media Foundation is a vibrant global network dedicated to strengthening the role of women in the news media worldwide as a means to further freedom of the press. The IWMF network includes women and men in the media in more than 130 countries worldwide. For more information, visit www.iwmf.org.


About the 2012 Courage in Journalism Award Winners

Reeyot Alemu, 31, worked as a columnist for independent Ethiopian newspaper Feteh until her arrest in June 2011. She was held without charge until September of that year, when she was accused of conspiracy to commit terrorist acts and participation in a terrorist organization. The Ethiopian government presented articles Alemu wrote criticizing its actions as evidence at her trial, as well as telephone conversations she had regarding strictly peaceful protests. 

Based on these materials alone, a judge sentenced Alemu to 14 years in prison. Prior to these events, Alemu was one of her country’s only female reporters who wrote critically about the political climate in Ethiopia, including analysis of government figures. Now, Alemu has fallen ill in prison. Her associates suffer harassment because of their connections with her. Despite this, Alemu has rejected offers of clemency in return for information about her colleagues.

Asmaa al-Ghoul, 30, is a blogger and freelance writer working in Gaza. Her stories analyze social and political life in the Middle East, focusing on the ongoing divisions among Palestinians and abuses of civil rights by both internal and external forces in Gaza. In 2007, al-Ghoul wrote an article in the form of an open letter to her uncle, a Hamas commander, questioning the methods of certain entities claiming to seek peace for Palestine. 

The article resulted in al-Ghoul’s uncle threatening to kill her. This is not uncommon: al-Ghoul regularly receives death threats against her own life and that of her young son. She has been beaten by Hamas security forces while covering popular protests and went through a period of sleeping in her office for fear of being killed on her way home.

Khadija Ismayilova, 35, is a reporter for Radio Free Europe/Radio Liberty’s Azerbaijani service. She investigates corruption and power abuse among her country’s elite. In May of 2012, Ismayilova became the target of a massive smear campaign threatening to defame her and put her life at risk unless she stopped reporting. This included an anonymous letter with photos from surveillance cameras planted in Ismayilova’s apartment, depicting her in an intimate situation with her boyfriend.

 It was made clear that she would stop her reporting, or risk having the photos made public. In the largely Muslim country of Azerbaijan, “honor killings” still occur. This is not the first time Ismayilova has been the subject of attempts to silence her. She is the victim of regular slander campaigns in pro-government media. The Azerbaijani president has personally tried to have her fired. During the many attempts to discredit her, Ismayilova has refused to stop working and has publicly denounced her accusers.

About the 2012 Lifetime Achievement Award Winner

Zubeida Mustafa, 70, is a Pakistani journalist who has worked for more than three decades at Dawn, one of Pakistan’s oldest and most widely circulated English-language newspapers. She was the first woman to work at the paper, which she did in the capacity of assistant editor and columnist. She helped to enact hiring policies favorable to women and promoted women’s equality in the newsroom. She has mentored dozens of young women in media and has spent her career writing serious and in-depth stories on issues including health care, economic inequality and political agency for women. Today, despite weakened eyesight, she continues to write prolifically and regularly contributes columns to Dawn.
  About the Awards

The IWMF Courage in Journalism Awards honor women journalists who have shown extraordinary strength of character and integrity while reporting the news under dangerous or difficult circumstances.



The Lifetime Achievement Award recognizes a woman journalist who has a pioneering spirit and whose determination has paved the way for women in the news media.Including this year’s award winners, 75 journalists have won Courage Awards and 21 journalists have been honored with Lifetime Achievement Awards. 

Source: IWMF



Thursday, May 3, 2012

መከላከያ ሰራዊቱ በርካታ የጋምቤላ ነዋሪዎችን ገደለ

ኢሳት ዜና:-
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጋምቤላ ክልል በፖከዲ መንደር ውስጥ 5 ሰዎችን መግደሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከማቾቹ ውስጥ አንድ መምህር፣ ሁለት ተማሪዎችና አንድ አርሶ አደር ይገኙበታል። 

የአይን ምስክሮች እንዳሉት በርካታ ተማሪዎች ተኩስ በተከፈተበት ወቅት ወደ ጫካ ገብተው የሸሹ በመሆናቸው የሟቾች ቁጥር ሳይጨምር አይቀርም። 

በጥቃቱ የቆሰሉትም በርካታ መሆናቸው ተገልጿል። በኮጎ ወረዳ ጋሀሪ በሚባል መንደር ደግሞ 4 ገበሬዎች ተገድለዋል። በአኮቦ ወረዳም እንዲሁ ወታደሮቹ የደቡብ ሱዳንን ድንበር ተሻግረው በጋምቤላ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት የጋምቤላ ህዝብ ሰሞኑን በሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲ ንብረት በሆነው በሳውዲ ስታር ኩባንያ ውስጥ ተቀጥረው ይሰሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ፓኪስታናዊያን ላይ የደረሰውን ጥቃት እንዲያወግዙ የተጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አስገራሚ ትእይንቶችን አሳይተዋል።

በሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪና የመንግስት ባለስልጣናት ይዘውት የወጡት መፈክር መለያየት፣ እንዲሁም ህዝቡ ንግግር ወደ ሚያደርጉት ወደ ክልሉ ፕሬዚዳንት ወደሆኑት አቶ ኦሞድ ኦቦንግ መጠጋት መጀመር ሰልፉ በ15 ደቂቃ ውስጥ እንዲበተን መደረጉን በስፍራው ተገኝቶ የተመለከተው ዘጋቢያችን  ኡጁሉ ኦሞት ገልጧል።

አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ” መለስ ዜናዊ በጋምቤላ ዙሪያ ምነው ቀበቶህን ፈታህ? ” የሚል መፈክር ይዞ የታየ ሲሆን፣ የመንግስት ባለስልጣናት ደጋፊዎች ደግሞ ልማታችን እና የሰፈራ ፕሮግራም በአሸባሪዎች ሊደናቀፍ አይችልም የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል።

ሰልፈኛው በስታዲየም እንዲሰባሰብ ከተደረገ በሁዋላ በመንግስት ባለስልጣናት የቀረቡትን መፈክሮች አብሮ እንዲያሰማ በሚጠየቅበት ጊዜ በተቃራኒው የራሱን መፈክሮች ማሰማት መጀመሩን ዘገባው ያመለክታል። ከደቂቃዎች በሁዋላም ሰልፈኛው “ጥያቄዎች አሉን ፕሬዚዳንቱን መጠየቅ እንፈልጋለን” ማለት ሲጀምር ፣ ባለስልጣናቱ ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን፣ የዛሬው ሰልፍ አላማ  መፈክሮችን ለማሰማት መሆኑን በመናገር ጥያቄዎችን ለመቀበል ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል።  

ሰልፈኛው ወደ ፕሬዚዳንቱ መጠጋት ሲጀመር ብጥብጥ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት ዝግጅቱ አልቋል እናመሰግናለን በማለት ፕሬዚዳንቱን ይዘው ሄደዋል። የመንግስት ሰራተኞች በግዴታ ወደ ሰልፉ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን፣ መፈክሮችም ተዘጋጅተው ነበር የቀረቡላቸው። ከፍተኛ ውጥረት በታየበት በዚህ ሰልፍ የከተማው ነዋሪዎች የሆኑ  የአኝዋክ ተወላጆች አለመገኘታቸው ታውቋል።

በጋምቤላ በዛሬው እለት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ታማኝ ምንጮችን በመጥቀስ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። በሌላ ዜና ደግሞ በቀርቡ በሳውዲ ስታር ሰራተኞች ላይ በደረሰው ጥቃት ቆስለው በመቱ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ከቆዩት ኢትዮጵያውያን መካከል አንደኛው ህይወቱ ማለፉ ተውቋል።

ከፌደራል መስሪያ ቤቶች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ጉድለት ተገኘ

 ኢሳት ዜና:-
የፌዴራል ዋና ኦዲተርየፌዴራል መ/ቤቶችን የ2003 የኦዲት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ለፓርላማ ይፋ በሆነው በዚሁ ሪፖርት መሰረት በድምሩ 151 ባለበጀት መ/ቤቶች ተካተዋል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው የጥሬ ገንዘብ ሒሳብ ትክክለኛነትን፣  አያያዝና አጠባበቅን ለማረጋገጥ ባደረገው ኦዲት 1 ቢሊየን 66 ሚሊየን  524 ሺ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተገኝቷል፡፡

 ከዚህ ሌላ በ59 መ/ቤቶች  ውስጥ  1 ቢሊየን 27 ሚሊየን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ በደንቡ መሰረት በወቅቱ  ሳይወራረድ ተገኝቷል፡፡ ትምህርት ሚ/ር በ 723 ሚሊየን 77 ሺ ብር፣ መከላከያ ሚ/ር  133 ሚሊየን 78 ሺ ፣ምርጫ ቦርድ 31 ሚሊየን 79 ሺ፣ ፣ፌዴራል ፖሊስ 23 ሚሊየን 99 ሺ ብር ያልተወራረደ ሂሳብ በመያዝ ቅድሚያውን ይዘዋል።

የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ ተመዝግቦ የተገኘ ሒሳብን በተመለከተ በ12 መ/ቤቶች 38 ሚሊዮን 66 ሺ ብር፣ በሌሎች 22 መ/ቤቶች ደግሞ ምንም ማስረጃ ሳይኖር  79 ሚሊየን 52 ሺ ብር በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል፡፡የተሟላ ማስረጃ ካላቀረቡት መ/ቤቶች መካከል መቀሌ የነቨርሲቲ፣ 23 ሚሊየን 34 ሺ ብር ፣ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን  6 ሚሊየን 77 ሺ ብር፣አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊየን 89 ሺ ብር ይገኙበታል፡፡

 የወጪማስረጃ ሳይቀርብ ገንዘብ ካወጡት መ/ቤቶች መካከል የአገሪቱን በጀትና  ፋይናንስ ይመራል የተባለው የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚ/ር ይገኝበታል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር 14 ሚሊየን 41 ሺ ብር ያለማስረጃ  ወጪ አውጥቷል፡፡ መከላከያ ሚ/ር፣ ጎንደር የኒቨርስቲ ፣ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፣ ገቢዎችና ጉምሩክ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቲር ያለማስረጃ  ገንዘብ  ወጪ በማድረግ ዋናው ኦዲተር ከሷቸዋል፡፡

ዋናው ኦዲተር በዚህ ሪፖርቱ ደንብና መመሪያን ባልተከተለ መልኩ 33 መ/ቤቶች  313 ሚሊየን 26 ሺ ብር  በማውጣት ግዥ ፈጽመው ተገኝተዋል ብሎአል፡፡  ከነዚህ መ/ቤቶች መካከል መቀሌ የኒቨርስቲ ፣ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፣ የኢንፎርሜሸንና ደህንነት ኤጀንሲ  ወይም የደህንነት  መስሪያ ቤት ይገኙበታል፡፡

ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ አለአግባብ በ26 መ/ቤቶች 237 ሚሊየን 16 ሺ ብር ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል፡፡ከነዚህም መካከል ጎንደር፣መቀሌ ፣ባህርዳር የኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አምና ዋና ኦዲተር ለፓርላማው ባቀረበው የ 2002 የኦዲት ሪፖርት በአመዛኑ በትምህርት ሚ/ር ሥር የሚገኙ ነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ሕግና ሥርዓትን ያልተከተሉ የሂሳብ አያያዝና ወጪዎችማሳየታቸው የሚታወስ ነው።
ህግና ስርአትን ባልተከተለ መልኩ በአንድ አመት ውስጥ ይህን ያክል ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች ሲወጣ፣ መንግስት አለ ያሰኛል ወይ በማለት አንድ የፓርላማ አባል ጠይቀዋል። ባልተወራረደ ሂሳብ ስም የሚወጣው ገንዘብ ለማመን አዳጋች ነው የሚሉት እኝሁ ሰው ለመሆኑ ጸረ ሙስና ኮሚሽንና የመንግስት ባለስልጣናት ለፌደራል ኦዲት ሪፖርት እውቅና ሰጥተው ምርመራ ያካሂዳሉ ወይስ እንደተለመደው ሪፖርቱ የሸልፍ ማሞቂያ ሆኖ ይቀራል ሲሉ ጥያቄያቸውን አክለዋል። 

ችግሩ ከአመት አመት እየተባባሰ መምጣቱ መንግስት ለፌደራሉ ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርት እውቅና እንደማይሰጥ እንደሚያመላክት እኝሁ ባለስልጣን ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጠዋል። አቶ መለስ በሰሞኑ የፓርላማ ንግግራቸው መንግስት አንድ እጁን ታስሮ ነው ሙስናን እየተወጋ  ያለው፣ የመንግስት ሌቦች አስገሩ በማለት መናገራቸው ይታወሳል።