Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, March 17, 2013

ሰበር ወሬ… ጣሊያንን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በገዛ መንግስታቸው ታሰሩ!

ነገሩን ድንገት ስለሰማነው ሰበር እንበለው እንጂ ወሬው እነኳ ቅስም የሚሰብር ነው፡፡ ዛሬ መጋቢት 8 2005 ዓ.ም በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች ጣሊያን ለጨፍጫፊው ግራዚያኔ ያሰራችውን ሀውልት ለመቃወም ከስድስኪሎ አደባይ እስከ ጣሊያን ኤንባሲ የመ፣ዘልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ተሰባስበው ነበር፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ገና ከመጀመሩ የደረሱት ፖሊሶች እጃቸው የገባውን ሀገር ወዳድ በሙሉ አስረው ወሰዱ፡፡ ከዛም በፖሊስ ጣቢያዎች ባሉ እስር ቤቶች ጨመራቸው፡፡


ከታሰሩት መካከል ዶክተር ያዕቆብ ሃይለማሪያም ይገኙበታል፡፡ በእውነቱ ይሄ እጅግ አስቂኝ እና እጅግም ቅስም ሰባሪ ዜና ነው፤”ጣሊያንን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በገዛ መንግስታቸው ታሰሩ!” ይህንን ማን ያምናል!? ባያምኑ ነው የሚሻለው ወዳጄ ላመንነውም ህመም ሆኖብናል!
ጥያቄ፤
እኔ የምለው… እንዴት ነመው ነገሩ ጣሊያን ከኢትዮጵያ አልወጣም እንዴ…?

Source: Abetockichaw blog

1 comment:

  1. Good question. ኖርዌይ ውስጥም ሳይኖር አይቀርም ።

    ReplyDelete