የምርጫ ምህዳሩን በማጥበብ ብቻውን ለአዲስ አበባ ምክር ቤትና ለአካባቢ ምርጫ የተዘጋጀው ኢህአዴግ የአዲስ
አበባ ከተማ አመራሮችን መመደቡንና ካንቲባም በስውር እንደሾመ ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት የዜና
ምንጮች አስታወቁ፡፡ ወ/ሮ ሀዜብ መስፍንም አዲስ አበባ ላይ ይወዳደራሉ፡፡
የዜና ምንጮቻች እንደሚናገሩት ኢህአዴግ የመንገድ ትራንስፖርት ሚንስትሩ አቶ ድሪባ ኩማን በከንቲባነት፣
የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳንና የግብርና ሚንስትሩ አቶ ተፈራ ደርበውን በም/ከንቲባነት መድቧል፡፡
የከተማ
ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌን የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ በስውር መሾሙን
የተናገሩት የዜና ምንጮቻችን፤ የጸጥታ ቢሮውንና የፖሊስ ኮሚሽነርነቱን አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ከአንድ የህወሃት
አመራር ጋር እንዲመሩት ተወስኗል፡፡
በተጨማሪም በከተማው አስተዳደር ውስጥ ያሉ ቁልፍ የስልጣን ቦታዎች ከህወሀት የሚወከል ባለስልጣን እንዲመደብ መወሰኑን የዜና ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ አመልክቷል፡፡ምንጮቻችን ጨምረውም በኢህአዴግ ም/ቤት ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ሲወስን የአቶ ድሪባ ኩማ ሹመት ሲቀርብ
ሰውየው “ምደባውን አልቀበልም ፤ በሚንስትርነት እቀጥላለሁ” በማለት ያነሱት ሀሳብ ተቀባይነት በማጣቱ ስብሰባውን
ረግጠው እስከመውጣት ደርሰው ነበር፤ ይሁን እንጂ ጊዜ ከወሰደ የማግባበት ሥራ በኋላ አቶ ድሪባ ምደባውን መቀበላቸው
ተነግቀሯል፡፡
አንዳንድ በኢህአዴግ ም/ቤት የተወከሉ የኦህዴድ ተወካዮች “ፓርቲያችን በፌዴራል ደረጃ የነበሩትን ቦታዎች እያጣ ነው” ሲሉ መተቸታቸውም ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የሟቹ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ሚስት ወ/ሮ ሀዜብ መስፍን ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ይወዳደራሉ የሚሉ
ጭምጭምታዎች ከኢህአዴግ መንደር መሰማቱን ተከትሎ ከንቲባነቱን ከሴትየዋ እንደማያልፍ የተለያዩ ግምቶች እየተሰጡ
ይገኛሉ፡፡
No comments:
Post a Comment