Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, January 10, 2013

የአላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ

alamata
ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል በአለማጣ ወረዳ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች  ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ያሉት ፣ የወረዳው የቤት አፍራሽ ግብረሀይል አባላት በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል ያሉዋቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሄዱበት ወቅት ነው።

ተማሪዎች፣ ህጻናት ፣ አዋቂዎች ከጧቱ 3 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሹ ድረስ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን የገለጡ ሲሆን፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ የሚተላለፉ መኪኖች  መተላለፊያዎች ተዘግተውባቸው ውለዋል።

Wednesday, January 9, 2013

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።

በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን  መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች  ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።

Tuesday, January 8, 2013

ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል

ከኢየሩሳሌም አርአያ
ሻለቃ ፀአዱ የህወሓት ታጋይ የነበረች ናት። ከኤርትራና ጣሊያን የዘር ግንድ ያላት ሻለቃ ፀአዱ የቀይ ቆንጆ ናት፤ ገፅታዋን በመመልከት ማንነትዋን በቀላሉ መገመት ይቻላል። የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባለቤት ነበረች። ሽማግሌው ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት የሚታወቁበት ባህርይ ሴሰኝነታቸው ነው። 

ከፀአዱ ጋር ከበረሃ የጀመሩት ፆታዊ ግንኙነት እስከ 1990ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ሲሆን በ <አብሮነት> ጊዜያቸው ልጆች አፍርተዋል። በኮንኮርድ ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ በሚገኘው የተንጣለለ ቪላ የሚኖሩት ሽማግሌው ስብሃትና ሻለቃ ፀአዱ ነጋ-ጠባ ሲያነታርካቸው የነበረው አስገራሚ « አጀንዳ» ፈንድቶ የወጣው ከላይ በተጠቀሰው አመት ነበር። በፓርቲው ሕግ፥ “አንድ የማ/ኰሚቴ አባል በትዳሩ ላይ ችግር ሲከሰት ጉዳዩ የሚታየው በድርጅቱ አመራር ነው”፤ ከዚህ ባለፈ ወደ ፍ/ቤት መሔድ አይቻልም።