Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, August 4, 2012

የሱዳን የደህነት አባላት የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅትን መሪ ልጅ አሰሩ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
መንግስት ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰራዊት አባላት ጋር ድርድር በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር።

ሱዳን አገር የሚገኙ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት የድርጅቱ ሊቀመንበር ባልተገኙበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ከመንግስት ጋር ድርድር አድርገዋል። መንግስት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ዩሱፍ ሀሚድ ወደ አገር ከገቡ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል መግባቱን ፣ ይሁን እንጅ አምባሳደሩ ማንኛውም ድርድር በሶስተኛ አገር መሆን አለበት በማለት ጠንካራ አቋም በመያዛቸው በድርድሩ አለመገኘታቸውን አምባሳደሩ ለኢሳት ገልጠዋል።

የትግል ጓዶቻቸው መሪው ባይሄዱም ልጃቸውን እንዲልኩላቸው ጠይቀዋቸው እንደነበር አምባሳደሩ ገልጠዋል። ልጃቸው ሀሊድ የሱፍ ሀሚድ ለእረፍት ወደ ሱዳን በተጓዘበት ወቅት የኢትዮጵያ የደህነት ሀይሎች በደማዚን ክፍለሀገር ወስደው እንዳሰሩት ተናግረዋል።

የደማዚን ክፍለሀገር አስተዳዳሪ የሆኑትን አሊህዲ ቡሽራን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ፣ አስተዳዳሪው ለማላውቀው ሚዲያ መረጃ መስጠት አልፈልግም በማለት መልሰዋል። አምባሳደር ዩሱፍ ከወራት በፊት ሰፊ ቃለምልልስ ለኢሳት መስጠታቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment