Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, August 14, 2012

ሰራዊቱ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ ነው

የኢሳት ዜና: የአቶ መለስ ዜናዊን መሰወር ተከትሎ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፤ ጦር ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲቆም የታዘዘው፤ በቅርቡ በተመሰረተውና በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት በጫረው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ (ነኢሰን) መግለጫ ጭምርም እንደሆነ አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ ገለጸ።

ለመከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሰረተበትን መግለጫ የበተነው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ፤ ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ውይይት እንደጫረና፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመኖር ታክሎበት ስጋት በመፍጠሩ ምክንያት፤ አየር ሀይሉን ጨምሮ የጦር ሰራዊቱ በሙሉ በአንደኛ ደረጃ በተጠንቀቅ እንዲቆም መደረጉ ታውቋል።


ባለፈው ሳምንት እንደዘገብነው፤ ለሰራዊቱ የአደገኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው፤ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ሊሰነዝሩ ስለመዘጋጀታቸው፤ መረጃ ደርሶናል በሚል ሰበብ ቢሆንም፤ የጦር ባለሙያዎች ለአክራሪዎች ጥቃት የአየር ሀይል በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ መቆም አሳማን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ለኢሳት ባለፈው ሳምንት በደረሰው መረጃ መሰረት፤ በዘመቻ መምሪያና በድርጅት መምሪያ ያሉ ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖች፤ 24 ሰኣታት ቢሮዎቻቸውን ክፍት አድርገው፤ በየተራ የበላይ ትእዛዝ እንዲጠባበቁ እንደተነገራቸው መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment