Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, August 14, 2012

ስደት መርረረን......ከጌዲዮን ደሳለኝ\ኖርዌይ\

ከጌዲዮን ደሳለኝ\ኖርዌይ\
ተሰደን ተሰደን አላልቅ ስላልን እንጂ በጣም ተሰደናል እኮ፥ አገራችንን ለቀን እየወጣን ለባዳ ሳናቀው እያስረከብን እኮ ነው፥፥
የድሮው የማናቀው የቅኝ ግዛት ታሪክ ተከረባብቶ ወደ ወደተስፋይቱ ምድር ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ከች እያለ ነው፥፥ እርግጥ ነው አንዳንዴም የመለስ ስርአት ሲመረን አንዳንዴም የነጮቹ ኑሮ ሲያስቀናን መጀመርያ ትዝ የሚለን ስደት ነው፥፥ 
አሁን አሁን ግን የምንሰደደው የሆነ ከአቅም በላይ ፍለፊታችን ግትር ያለ የሰይጣን ተራራ የሚሉት አይነት ባላንጣ የቆመ መሰለኝ፥፥ እኛም ደሞ ተልፈስፍሰናል፥ ምን እንደምንፈልግ እንኩአን ያወቅነው አልመሰለኝም፥፥ ሰይጣኑን በማስወጣት ፈንታ ለሰይጣኑ መገበር ጀምረናል፥፥

ሁሉም ተቃዋሚ ነኝ ይላል ፥ ሁሉም መለስን ለማውረድ እሰራለው ይላል፣ ሁሉም ስለአንድነት ያወራል,፣፥ ግን ደሞ አብሮ ለመስራት የራሱ ፕሮግራምን ብቻ የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮግራም አርጎ ያያል፥፥ ይሄን ያህል አመታቶች በነጮቹ አገር እየኖርን እንኩአን ከነሱ ለመማር አልቻልንም,፣ ነው ወይስ እኛ ልንከተል የምንፈልገው የፖለቲካ አይነት ገና አልተፈተረም፥ ነው ወይስ አስማት ነው የምንፈልገው፥፥ 
እኔ በበኩሌ ስለወያኔ መስማት ሰለቸኝ እንዴ አስቡት እስኪ እኔ በአንድ የኖርዎይ  ጋዜጣ ላይ እንዳነበብኩት እንግዲህ ወያኔ ወይም ወይ ያኔ በ1997 ምርጫ ላይ የነበረው የደጋፊ ብዛት 800000 ነበር አሁን ኦፊሻሊ የሚታወቀው ወደ 3 000 000 ደጋፊ እንዳላቸው ነው፣ እሱም በተለያያ መንገድ በነጋዴው ላይ በተማሪው ላይ በሰራተኛው ላይ በሚደርሱ የተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ነው የሚል የራሴ ከፍተኛ እምነት አለኝ፥፥ ከነዚህም ውስጥ ደሞ ሆዳም ለሆዱ አዳሪ የሆነው ይበዛል ባይ ነኝ፣፥ እንኩአን መለስ ሃሳብ ሰቶ አደለም ሃሳብ ለመስጠት ሲያስብ ሆዳሞቹ ሁለት እጃቸውን ሊያወጡ ይችላሉ ድሮ ልጅ እያለን በቀደመ በቀደመ እያልን እንደተጫወትነው ማለት ነው፥፥ በቻ ባጭሩ ቁጭ ብሎ መደናነቅ ነው፥ 
ያም ሆነ ይህ ግን አስቡት ይሄ ማለት ግን ወያኔ በውነት ሃይል ስላለው አደለም እየገዛን ያለው እኛ አሜን ብለን ስለተገዛንላቸው ነው እንጂ፥ ወያኔ እንዲወርድ ብንፈልግም  ዳሩ ግን ታግለን ሳይሆን ተአምር ወይም አስማት እንጠብቃለን፥፥
አንዳንዱ ወያኔን በጣም ይጠላል ግን ደሞ መቃወም ያስብና አገር ቤት መስራት የጀመርኩት ቤት ጭቃው ተለጥፎ ሳያልቅ ፣ ለክረምት ሂጄ ቤተሰቤን ሳላይ፥ አዲስ  አበባ ናፍቃኛለች ምናምን ወይም ደሞ ወገቤን መቀነት ሳልታጠቅ ቀርቼ ነው ሃተታ ያበዛል፥ ሌላው ደሞ ጠንካራ የተቃዋሚ መሪ የለም ይላል፥፥ 
እና ምን ይሻላል
አሁን ደሞ አዲሱ ወሬ መለስ ሞተ ሞተ ሞተ ሆንዋል፥ በረከት ምን ነካው ለምን ለኢትዮጵያ ህዝብ አይነግረንም ለምን ያጉአጓናል ልብ ሰቀላ መሆኑ ነው ኡኡቴ አሉ ወይዘሮ ማዘንጊአ፥፥ የሚገርመው አገር ቤት ያለው ህዝብ የሚሰማበት አጋጣሚ በጣም ጠባብ መሆኑ ነው፥፥ ግን እኮ ደሞ መለስ ብቻውን አልነበረም 21 አመት ሙሉ ሲነዳን የኖረው፥ አሁንስ ሌላ ሰው እንደማይነዳን ምን ማረጋገጫ አለን፥፥ አያድርገውና የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አሁን መለስ ገሃነምን ድል አርጌ መጣው ቢል እንደገና ተረጋግተን ቁጭ ልንል ነው፥፥እኛ ብንፈዝም ኢትዮጵያን ግን ሁሌም እግዚአብሄር ያያታል፥
አሜን

No comments:

Post a Comment