Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, June 2, 2012

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሁለት የተቃዋሚ ፓርተዎች አባላትን አፍነው ወሰዱ

ኢሳት ዜና:-
የኢሳት የደባርቅ ወኪል ባስተላለፈው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት ቀድሞ የመኢአድ አባል የነበረውና በምርጫ 97 ቅንጅትን፣ በምርጫ 2002 ደግሞ አንድነት ፓርቲን በመወከል ሲንቀሳቀስ የነበረውን አቶ ስለሺ ጥጋቤን አፍነው ወስደውታል።

ግለሰቡ ከተያዘ በሁዋላ ቤቱ ለ2 ሰአታት ሲበረበር እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።  የአቶ ስለሺ ጥጋቤ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጡት፣ ፖሊሶች እና የደህንነት ሰዎች ግለሰቡን አፍነው ወደ አዲስ አበባ ወስደውታል።

በጭልጋ ወረዳ ደግሞ የመኢአድ አደራጅ የሆነው አቶ መለሰ አስሬ ትናንት ቤቱ ሲፈተሽ ከቆየ በሁዋላ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል። ግለሰቦቹ ታፍነው ስለተወሰዱበት ምክንያት እና የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። አንድነት ፓርቲም ሆነ መንግስት በግለሰቦቹ መታሰር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የለም።

ይሁን እንጅ ዘጋቢያችን እንደሚለው ከዋልድባ ገዳም እና ከራስ ዳሸን  ጋር በተያያዘ በአካባቢው ከሚታየው ውጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የደባርቅ ወረዳ ወጣቶች ከዋልድባ፣ ከራስ ደጀን እንደሁም ከመልካም አስተዳዳርና ፍትህ እጦት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ እንደሚላተሙ ይታወቃል።

 የደባርቅ መምህራን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን በማለት ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። በጭልጋ ወረዳም እንዲሁም መምህራን የስራ ማቆም እድማ ማድረጋቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment