Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, May 29, 2012

የአቶ መለስ ምስል ከአደባባይ ተሰረቀ


Source: Finote Netsanete
በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡

 በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስል “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግና” የሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ተናግሯል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ገለፁት ምስሉ ተተክሎ የቆየው ለአምስት ቀናት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የምስሉን መጥፋት ግራ አጋቢ ያደረገው የአቶ መለስ ፎቶ በላዩ ላይ የታተመበት ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን መሰረቁ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአቶ መለስን ተክለ ስብዕና የሚገነቡ ምስሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተበራክተዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ በየትኛውም የአቶ መለስ ምስል ላይ ጉዳትም ሆነ ጥፋት ደርሶ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ ለምስሉ ከ35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ) ብር በላይ ማውጣቱን ገልፃóል፡፡ አቶ ኢሳያስ ክሎም 28 ካሬ የሚሆነው ይህው ምስል በመጥፋቱ እንደተደናገጠ ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡

ይኽው የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምስል ከተሠቀለበት ቦታ ተገንጥሎ የተወሰደ ሲሆን በዘመናዊ ዲጂታል የህትመት መሣሪያ በኢሣያስ ማስታወቂያ ታትሞ በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢሳያስ ማስታወቂያ ባለቤት ወጣት ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገረው የምስሉ መጠን 7 ሜትር በ4 ሜትር መሆኑን በመግለፅና ስራውን ለእይታ ለማብቃትና አጠቃላይ የፍሬም ሥራውን በማካተት 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ወጭ እንደተረገበት ገልፃóል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚኒስትሩ ምስል ግዙፍ ሆኖ ከፊት ለፊት አሁን በመገንባት ላይ ያለው
የህዳሴው ግድብ በአንድ ላይ ሆኖ ከምስሉ ስር “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ
ጀግና” የሚል ፅሑፍ እንደነበረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment