Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, December 7, 2012

የሰሞኑ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትና ፖለቲካ

ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።
 
Rene Lefort ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይን ላይን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰሞኑን የተሰጠውን ሶስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ። በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደገና የመንግሥቱን ስልጣን እየተቆጣጠሩ ናቸው ያሉትንም ያብራራሉ። ስለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዕድገት አሃዝና የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አንድምታ በተመለከተ አውስተዋል።


Lefort ከሰሃራ በታች ያሉትን የአፍሪካ ሀገሮች በተመለከተ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1970ዎቹ ጀምረው Le Monde - Le Monde Diplomatique  እና በመሳሳሉት ጋዜጦች ጽሁፎችን ሲያወጡ ቆይተዋል። በ1982 ዓም Ethiopia A Hretical Revolution የተሰኘ መጽሐፍም ደርሰዋል።

“ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሃት ውስጥ በኦፊሴል ሁለተኛው ሰው ናቸው። ሐቁ ግን ዋናው የፓርቲው መሪ እሱ ነው ምክንያቱም አባይ ወልዱ በጣም አቋመ ጥብቅ ሰው አይደሉም። አሁን ደብረጽዮን የምጣኔ ሃብት ዘርፍ ጠቅላላ ኃላፊ ሆኗል። ይሄ እንግዲህ የደህንነት አገልግሎቱ አንዱ ዋና ባለልጣን ከመሆኑ በተጨማሪ ነው።” የሚሉት Lefort “ከህወሃት እጅ ውጪ ያለ አንድም ዋና የስልጣን ቦታ አይታየኝም፤” ይላሉ።

የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚው Rene Lefort በዚሁ የቅርብ ጊዜ ጽሁፋቸው መነሻነት ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።


 

ከሠሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪካ ሃገሮችን በተመለከተ በሚያደርጓቸው ምርምሮችና ዘገባዎች በዋናነት ከሚታወቁት ተንታኞች አንዱ የሆኑት ሬኔ ለፎር በቅርቡ “መለስ ከመቃብር እየገዙ ነው። ግን እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ፅሁፍ አስነብበዋል፡፡

ሬኔ ለፎር ከቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሰሞኑን የተሰጠውን ሦስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ፡፡

“በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች የመንግሥቱን ሥልጣን እንደገና እየተቆጣጠሩ ናቸው” በማለት ያብራሩበትንና ተዛማጅ ጥያቄዎችን የመለሱበትን የመጀመሪያ ክፍል ቀደም ሲል አቅርበናል።

የመጨረሻውን ክፍል ያዳምጡ፤ ቆንጂት ታየ ነች ያቀናበረችው።\


No comments:

Post a Comment