Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, August 23, 2012

የተለያዩ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ዙሪያ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው

ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር ታጋይ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለአቶ መለስ ዜናዊ ወታደራዊ ትምህርት እንደሰጡዋቸው  ይናገራሉ::

የአቶ መለስ ዜናዊን የ21 አመታት አስተዳዳር እንዴት ይገመግሙታል ተብለው የተጠየቁት አቶ አስገደ ፣ በርካታ ችግሮች መታየታቸውን አልሸሸጉም::


አቶ መለስ ስልጣን ለቀው ያሳለፉትን አመራር ለመገምገም እድል አግኝተው ቢሆን ኖሮ ይመርጡ እንደነበር ተናግረው፣ ስልጣኑን የተረከበው አካልም የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ይመክራሉ::

የግንቦት 7 ከፍተኛ የአመራር አካል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜናዊ ስራዎች በተጨባጭ መመዘን እንዳለባቸው እና ሀዘኑም ምስጋናውም ከዚያ ጋር መታየት እንዳለበት ይገልጣሉ::

በኢትዮጵያ  የተሻለ ስርአት ለመገንባት ፖለቲካው ሊለወጥ እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸው ይናገራሉ::

No comments:

Post a Comment