Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, August 19, 2012

ኢቲቪ የኢድን ቀጥታ ዝግጅት ሳያልቅ አቋረጠ!

Abe Tokichaw: ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሶስት ቀን ጀመሮ የረመዳን ፆም ፍቺን አከባበር አስመልክቶ በዜና ዘገባው ላይ ረጅም ሰዓት ሰጥቶ ሲዘግብ ሰንብቷል። ከዛም አልፎ ተርፎ ገና ከሶስት ቀን አንስቶ በየዜናዎች መሀከል  በረጅሙ፤“እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ!” የሚል መልዕክት ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ደግሞም የተለያዩ ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎችን በዓሉን እንዴት “ሰላማዊ በሆነ መልኩ” እንደሚያከብሩት ሲጠይቅ እና ሲጨነቅ ሰንብቷል።
እኔን ጭንቅ ይበለኝ…!


ሁላችንም የምናውቃት አንድ አባባል አለች “ጥንቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ!” የምትል። “ጎረምሳው” መንግስታችን ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጋር የታጋባውን እልህ ለምን በሰከነ አዕምሮ ምላሽ ለመስጠት እንደማይሞክር ይደንቃል። ወይስ ስልጣን ላይ ያለ ሰው የሰከረ እንጂ የሰከነ አዕምሮ የለውም? እንደርሱም ከሆነ ሽሮ ፍትፍት በልቶ ሞቅታውን በረድ አድርጎ ድጋሚ ሰከን ብሎ ቢያስብ እና የሙስሊም ወዳጆቻችን ጥያቄን በአግባቡ ቢመልስ ለራሱም ከአጓጉል ጭንቀት ይድናል እኛም ሌሎች ጨዋታዎችን ለመጫወት ዕድል እናገኝ ነበር።

የሆነ ሆኖ የሙስሊሙን ተቃውሞ ማየት ሲያስፈራው የሰነበተው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዛሬው ዕለት ከአዲሳባ ስታድየም ከአዳማ እና ከጅማ የኢድን ክብረ በዓል ከየስፍራዎቹ በቀጥታ አስተላልፊያለሁ ብሏል። “የቀጥታ ፕሮግራሙ” ሲተላለፍ በተለይ የአዲስ አበባው በኢሊኮፍተር የተነሳ የማይንቀሳቀስ ፎቶ የሚመስል ነገር ለረጅም ሰዓት ከበዓሉ ጋር ምንም ግንኙነት በሌለው ሙዚቃ ታጅቦ ሲታይ ነበር። ከዛም ተመስገን ሁለት ሰዓት ሆነና ዜና ይዞ ቀረበ በዛውም የኢድ ቀጥታ ዝግጅቱ ተቋረጠ! ወዳጆቼ እንደጠቆሙኝ ከሆነ የቀጥታ ስርጭቱ የተቋረጠው ተቃውሞው በማየሉ ነበር።
ልክ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራም እያሳየ ነው…!

No comments:

Post a Comment