Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, July 25, 2012

በመልጋ ወረዳ በተነሳ ግጭት ከ19 በላይ ፖሊሶች በጽኑ ቆሰሉ

ኢሳት ዜና:-ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ  በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል።

አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር። በገበያ ላይ የነበረው የአካባቢው ህዝብ ባገኘው መሳሪያ ሁሉ በመጠቀም ከፖሊሶች ጋር ግብ ግብ የገጠመ ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች፣ አፈሙዛቸውን ወደ ፖሊሶች በማዞር በርካቶችን አቁስለዋል።


ከተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች የተውጣጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ደርሰው በህዝቡ ላይ በከፈቱት ተኩስ ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን ለማብረድ የቻሉት ከአጎራባች ወረዳዎች የፌደራል ፖሊስ አባላትን በብዛት በማምጣት ነው።

ፖሊሶቹ ዛሬ በእየቤቱ አሰሳ በማድረግ አንዳንድ ወጣቶችን እየያዙ ወደ እስር ቤት ወስደዋል። በአካባቢው ያለው ውጥረት እየጨመረ፣ የአካባቢው ሰውም ራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚችለበትን መሳሪያ ሁሉ ማዘጋጀቱን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት።

የሲዳማ ተወላጆች ካለፈው ወር ጀምሮ መብታችን ይከበር፣ የክልል አስተዳዳር ይሰጠን የሚሉ ጥያቄዎችን በማቅረብ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲወዛገቡ እንደነበር ይታወቃል።

የመልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ያቀረብነው ጥያቄ በአግባቡ እስካልተመለሰ ድረስ፣ መንግስት አለ ብለን ግብር ለመክፈል እንቸገራለን በማለታቸው ነው የትናንትው ግጭት የተነሳው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለክልሉ መንግስት እውቅና እንደማይሰጡ እና ግብር እንደማይከፍሉ ሲናገሩ መሰማታቸውን ዘጋቢአችን ገልጧል።

No comments:

Post a Comment