Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, May 17, 2012

ማህበረ ቅዱሳንን በመንግስት የማስመታቱ ሴራ ቀጥሏል

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ማህበረ ቅዱሳን በሚያሳትማቸው ልሳኖቹ በዋልድባ በሚገነባው የስኳር ፐወሮጀክት ዙሪያ መንግስትን የሚደግፍ ዘገባ ያላተመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ  በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ተጠየቀ።

በቤተ- ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ለማህበሩ በፃፈው ክስ አዘል ደብዳቤ፦ “በዋልባ ገዳም አካባቢ የሚካሄደውን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በተመለከተ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያወጣው መግለጫ በማኅበሩ ልሳናት ላይ ለምን እንዳልተዘገበ  ማህበሩ  በጽሁፍ መልስ ይሰጥበት ዘንድ ጠይቋል።

ከስኳር ኮርፖሬሽን ሚኒስትሩ ከ አቶ አባይ ፀሀዬ ጋር ወደ ዋልድባ ሄደው የነበሩት የቤተ-ክህነት ተወካዮች ከጉዟቸው መልስ በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ፤ እየተካሄደ ያለው የስኳር ፕሮጀክት የዋልድባን ገዳም ይዞታ እንደማይነካ፤ ይልቁንም የፕሮጀክቱ ግንባታ ለመነኮሳቱ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፃቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ለተለያዩ ሚዲያዎች ፍጆታ እንዲውል በማለት በጽሁፍ የበተኑትም ጋዜጣዊ መግለጫ በቴሌቪዥን ቀርበው የተናገሩትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የገዳሙ መነኮሳት እና የ አካባቢው ነዋሪዎች  የ አቶ አባይ ፀሀዬም ሆነ የቤተ-ክህነት ተወካዮቹ መግለጫ ውሸት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ።

የቤተ-ክህነት ወኪሎች ወደ ዋልድባ ባቀኑበት ወቅት የማህበረ-ቅዱሳን ጋዜጠኞችም  ሁኔታውን ተከታትለው  ለመዘገብ ወደ ስፍራው ያመሩ ሲሆን፤ ከጉዟቸው መልስ ግን  “የቤተ-ክህነት ሰዎች ስለሰጡት መግለጫም “ሆነ  “ራሳቸው በአካል ስላዩት እውነታ” ከመፃፍ ተቆጥበዋል።

የማህበሩ ልሳናት ጋዜጠኞች ስላዩት እውነታ ከመዘገብ የተቆጠቡት፤ጋዜጠኞቹ ያረጋገጡት ነገር የመንግስት ባለውልጣናት እና የቤተ-ክህነቱ ተወካዮች ከሰጡት መግለጫ ጋር የሚጋጭ  ነው።የቤተ-ክህነቱ ተወካዮች የሰጡት መግለጫ በውሸት የታጀለ ነው። የስኳር ፕሮጀክቱ ጠቀሜታው ባይስተባበልም፤ የገዳሙን ህልውና አጠያያቂ አድርጎታል።የተረጋገጠው እውነታ ይኸው ነው።

ልሳናቱ  ቢዘግቡ ይህን ነበር የሚዘግቡት። ይህን ከመዘገብ የተቆጠቡት መንግስትና አንዳንድ የማህበሩ ፀሮች ማህበሩን በፖለቲካ ጠምዝዞ ለመጣል እያደረጉት ላለው ሴራ በር ላለመክፈት ነው” ብሏል-አንድ ስሙን መግለጽ ያልፈለገ የማህበሩ አባል ለኢሳት በሰጠው አስተያዬት።

”…ይሁንና ይህን ያህል ጥንቃቄ ቢደረግም ይባስ ብሎ የሀሰት መግለጫ ለምን አልተዘገበም?” የሚል ክስ አዘል ጥያቄ መቅረቡ አስገራሚ ነው”ያለው ይኸው የማህበሩ አባል፤ “ማህበሩ በነሱ ሥልጣን ስር ስለሆነ በሚያትማቸው ጋዜጦች የነሱ ሀሰብ ግዴታ መውጣት እንዳለበት ማሰባቸውም፤እጅግ አደገኛ የአፋኞች አስተሣሰብ ነው”ብሏል።

ሌላው አስገራሚው  በጠቅላይ ቤተ-ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ በመምህር ዕንቁ-ባህርይ ተከስተ  ስም እና ፊርማ  ለማህበረ-ቅዱሳን ጽህፈት ቤት የተፃፈው ክስ አዘል ደብዳቤ ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከፓትርያርኩ ጽህፈት ቤቶች በተጨማሪ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ግልባጭ መደረጉ ነው።

ቀደም ሰል የህወሀቱ መስራች አቦይ ስብሀት ነጋ እና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አባይ ፀሀዬ የማህበረ ቅዱሳንን አመራሮች ቢሯቸው ድረስ ጠርተው ማስፈራራታቸው፤ በቅርቡ ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላ ሪፖርት ሲያቀርቡ ማህበሩን የአክራሪዎች ስብስብ እንደሆነ አስመስለው መዝለፋቸው ይታወሳል።

1 comment: