Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, May 15, 2012

በበለደ ወይን የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በሶማሊያ በበለደወይን አካባቢ በመንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል።

 ፍንዳታው የተከሰተው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ፣ ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ለማምራት ጉዞ ሲጀምር ነው። ምንም እንኳ የሟቾች ቁጥር ባይገለጠም፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ሁለት ሲቪሎችን መግደላቸው ታውቋል። 

እስካሁን ድረስ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰው አልታወቀም። የኢትዮጵያ ወታደሮች አካባቢውን አጥረው ፍተሻ መጀመራቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment