Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, May 3, 2012

ከፌደራል መስሪያ ቤቶች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ጉድለት ተገኘ

 ኢሳት ዜና:-
የፌዴራል ዋና ኦዲተርየፌዴራል መ/ቤቶችን የ2003 የኦዲት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ለፓርላማ ይፋ በሆነው በዚሁ ሪፖርት መሰረት በድምሩ 151 ባለበጀት መ/ቤቶች ተካተዋል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው የጥሬ ገንዘብ ሒሳብ ትክክለኛነትን፣  አያያዝና አጠባበቅን ለማረጋገጥ ባደረገው ኦዲት 1 ቢሊየን 66 ሚሊየን  524 ሺ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተገኝቷል፡፡

 ከዚህ ሌላ በ59 መ/ቤቶች  ውስጥ  1 ቢሊየን 27 ሚሊየን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ በደንቡ መሰረት በወቅቱ  ሳይወራረድ ተገኝቷል፡፡ ትምህርት ሚ/ር በ 723 ሚሊየን 77 ሺ ብር፣ መከላከያ ሚ/ር  133 ሚሊየን 78 ሺ ፣ምርጫ ቦርድ 31 ሚሊየን 79 ሺ፣ ፣ፌዴራል ፖሊስ 23 ሚሊየን 99 ሺ ብር ያልተወራረደ ሂሳብ በመያዝ ቅድሚያውን ይዘዋል።

የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ ተመዝግቦ የተገኘ ሒሳብን በተመለከተ በ12 መ/ቤቶች 38 ሚሊዮን 66 ሺ ብር፣ በሌሎች 22 መ/ቤቶች ደግሞ ምንም ማስረጃ ሳይኖር  79 ሚሊየን 52 ሺ ብር በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል፡፡የተሟላ ማስረጃ ካላቀረቡት መ/ቤቶች መካከል መቀሌ የነቨርሲቲ፣ 23 ሚሊየን 34 ሺ ብር ፣ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን  6 ሚሊየን 77 ሺ ብር፣አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊየን 89 ሺ ብር ይገኙበታል፡፡

 የወጪማስረጃ ሳይቀርብ ገንዘብ ካወጡት መ/ቤቶች መካከል የአገሪቱን በጀትና  ፋይናንስ ይመራል የተባለው የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚ/ር ይገኝበታል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር 14 ሚሊየን 41 ሺ ብር ያለማስረጃ  ወጪ አውጥቷል፡፡ መከላከያ ሚ/ር፣ ጎንደር የኒቨርስቲ ፣ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፣ ገቢዎችና ጉምሩክ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቲር ያለማስረጃ  ገንዘብ  ወጪ በማድረግ ዋናው ኦዲተር ከሷቸዋል፡፡

ዋናው ኦዲተር በዚህ ሪፖርቱ ደንብና መመሪያን ባልተከተለ መልኩ 33 መ/ቤቶች  313 ሚሊየን 26 ሺ ብር  በማውጣት ግዥ ፈጽመው ተገኝተዋል ብሎአል፡፡  ከነዚህ መ/ቤቶች መካከል መቀሌ የኒቨርስቲ ፣ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፣ የኢንፎርሜሸንና ደህንነት ኤጀንሲ  ወይም የደህንነት  መስሪያ ቤት ይገኙበታል፡፡

ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ አለአግባብ በ26 መ/ቤቶች 237 ሚሊየን 16 ሺ ብር ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል፡፡ከነዚህም መካከል ጎንደር፣መቀሌ ፣ባህርዳር የኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አምና ዋና ኦዲተር ለፓርላማው ባቀረበው የ 2002 የኦዲት ሪፖርት በአመዛኑ በትምህርት ሚ/ር ሥር የሚገኙ ነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ሕግና ሥርዓትን ያልተከተሉ የሂሳብ አያያዝና ወጪዎችማሳየታቸው የሚታወስ ነው።
ህግና ስርአትን ባልተከተለ መልኩ በአንድ አመት ውስጥ ይህን ያክል ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች ሲወጣ፣ መንግስት አለ ያሰኛል ወይ በማለት አንድ የፓርላማ አባል ጠይቀዋል። ባልተወራረደ ሂሳብ ስም የሚወጣው ገንዘብ ለማመን አዳጋች ነው የሚሉት እኝሁ ሰው ለመሆኑ ጸረ ሙስና ኮሚሽንና የመንግስት ባለስልጣናት ለፌደራል ኦዲት ሪፖርት እውቅና ሰጥተው ምርመራ ያካሂዳሉ ወይስ እንደተለመደው ሪፖርቱ የሸልፍ ማሞቂያ ሆኖ ይቀራል ሲሉ ጥያቄያቸውን አክለዋል። 

ችግሩ ከአመት አመት እየተባባሰ መምጣቱ መንግስት ለፌደራሉ ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርት እውቅና እንደማይሰጥ እንደሚያመላክት እኝሁ ባለስልጣን ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጠዋል። አቶ መለስ በሰሞኑ የፓርላማ ንግግራቸው መንግስት አንድ እጁን ታስሮ ነው ሙስናን እየተወጋ  ያለው፣ የመንግስት ሌቦች አስገሩ በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment