Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, March 17, 2013

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ: ኢትዮጵያ

ARCHIV - Pakistanische Journalisten protestieren in Karachi gegen die Behinderung ihrer Arbeit (Archivfoto/Illustration vom 16.03.2007). Die Vereinten Nationen begehen auf Initiative ihrer Kulturorganisation UNESCO seit 1994 jährlich am 3. Mai den Tag der Pressefreiheit. Foto: Nadeem Khawer (zu dpa-Themenpaket vom 28.04.) +++(c) dpa - Bildfunk+++
pixel

የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ስሞታ ያቀርባሉ ።አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የውጭ መንግሥታት የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ በተለያዩ ጊዜያት በሚያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እነዚህን ዘገባዎች አይቀበልም ። ይልቁንም በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። 


ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች መብቶችን በሚጥሱ ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶችና የውጭ መንግሥታት እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስሞታ ያቀርባሉ ። እነዚህ ወቀሳዎች የሚቀርቡበት መንግሥት በቅርቡ «ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር » ያለውን ሠነድ አዘጋጅቷል ። 

በተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህ የድርጊት መርሃ ግብር ፋይዳ ና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩልን አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ አቶ እንዳልካቸው ሞላ በቀድሞው አጠራሩ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ተመራማሪን ጋብዘናል ። ሙሉውን ውይይቱን ያድምጡ

No comments:

Post a Comment