Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, March 17, 2013

መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ

መኢአድ
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ  ” በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው  አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ጨም     ሮ በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እያፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡን ” ገልጿል።

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተማዎች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የባንክ ብድርን ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ተድርጓል ብሎአል መኢአድ በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በባህርዳር ያለመጣለያ በጎዳና እየኖሩ መሆኑን መኢአድ በመግለጫው አመልክቷል።በባህርዳር ለጎዳናና ተዳዳሪነት ከተዳረጉት መካከል ብዙ ነፍሰጡሮችና ህጻናት የገኙበታል።


አገዛዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ በብሄራዊ ጨቋኝነት በመፈረጁ በአርባ ጉጉ ፣ በበበደኖ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በጋምቤላ እንዲጨፈጨፍ ሲያድረጉ አገዛዙ ምን ያክል የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለማጥፋት እንደፈለገ አመለካች ነበር፣ የሚለው መኢአድ፣  ከአንድ አመት በፊት በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በከፍተኛ ጭካኔ በአማርኛ ተናጋሪ አርሶአደር ፣ ሴቶች፣ ነፍሰ ጡር፣ ህጻናት እና ሽማግሌዎች ላይ የተጀመረው ጭካኔ የተሞላበት ስደት ተባብሶ ቀጥሎ በየጎዳናው የሚጣለው የኔቢጤ ከመሆን አልፎ ለአውሬና ለአሰቃቂ ኑሮ የተጋለጠው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህብረተሰብ ቁጥር እየጨመረ በቤንሻንጉል ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር እና በአንዳንድ የአሮሚያ ክልል እየቀጠለ ነው ብሎአል፡፡

መኢአድ ” ማንኛውም ሰው በቋንቋው ፣ በጎሳው፣ በእምነቱ፣ በቀለሙ እና በማንኛውም ልዩነት ምግብ ሲያጣ መጠለያ ሲነፈገው ጨቅላ ህጻናት በየጎዳናው ሲሞቱ፣ ነፍሰጡሮች በየበረንዳው ሲወድቁ፣ ህሊናን የሚያደማ መሆኑን ገልጾ፣ የህንን ጨቋኝ ስርአት በአለም ህዝብ ፊት በዘር ማጥፋት ወንጀል ልንከሰው ይገባል ብሎአል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ  ከ5 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እንዲፈናቀሉ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የተባሉ የ67 አመት አዛውንት ” ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን  ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። “በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አፍርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡” ብለዋል።

” እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ አስረድተዋል።

ጎስቋላዋ የ67 ዓመት እናት በማያያዝም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ እንዳልን፤ አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት  በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡ ፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡ ፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ  “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ ፣ ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ግርማ የተባለ ወጣት፣ ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡  ሳትሞት ሆስፒታል ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ አትታከም እንጂ ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡

አዛውንቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ሲገልጹ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡ ፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር አንድ ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡ ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ 

በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረር በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ፣ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡ ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ ካሳ እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡ ፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ማቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment