Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, November 16, 2012

በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱን ጮህቱም ሰሚ ማጣቱን አንዲት የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ። ሥለችግሩ ብናነሳም የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ምን አገባችሁ በሚል መሳለቂያ ያረጉናል ሲሉም ምሬታቸውን ሲገልጹ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታይተዋል።


የዲሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈጻሚ ተቋማት ኋላፊነት በሚል ርዕስ ባጠቃላይ በሚንስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ ይህንን የተናገሩት የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ናቸው።  በመንግስት የተቋቋመው የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር የተሾሙት  በጠ/ሚንስትሩ አቅራቢነት በፓርላማ ሲሆን ሕዝቡ ብቻ ሣይሆን እኛም ሰሚ አጥተናል ሲሉ በሚከተለው ሁኔታ ገልጸዋል።

‘’ሕዝብ ተማሯል እንባውን እንዲያብስለት የተቋቋመው የእንባ ጠባቂ ተቋምም ሰሚና አድማጭ አላገኘም ምን አገባችሁ እየተባልን የሥራ አስፈጻሚው መሳቂያ ሆነናል ሲሉ መናገራቸው በኢትዮጲያ ቴለቪዥን በድምጽና በምስል ቀርቧል።’’

ከኢትዮጲያ ቴለቪዥን ተውስዶ ሐገር ቤት በሚታተመው ሠንደቅ ጋዜጣ ላይ ጭምር የሰፈረው የወ/ሮ ፎዚያ አሚንና የሌሎች ባልስልጣናት አስተያየት በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት እንዳይካሄድ መደረጉን በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላም ሲሸጋገር ቆይቶ ዘግይቶና ይተላለፋል ባልተባለበት ቀን መተላለፉ ከሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ መረዳት ተችሏል። 

የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕውሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አባይ ፀሐዬ የሕውሐት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ዶር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተመሳሳይ ችግሮች መኖራቸውን አስታውቀዋል። 

በተለይም የስኳርኮርፖሬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ የመንግስት ተቋማትን ለመቆጣጠር የሚደረገው እንቅስቃሴ አጥጋቢ አይደለም ብለዋል እነዚህ ተቋማት ግንዱን ትተው ቅርንጫፎቹ ላይ ይረባረባሉሲሉም ተችተዋል። Listen to the ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 14 2012 Ethiopia.



No comments:

Post a Comment