Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, November 16, 2012

በኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው ችግር እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት   አሁንም በችግር  እየታመሰ ነው፡


የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በሀረሪ ክልል የሚገኙ አንዳንድ የኦህዴድ ባለስልጣናት ከሀላፊነት ተነስተዋል።

ኦህዴድ ካካሄደው ግምገማ በሁዋላ የተባረሩት ባለስልጣናት አብዛኞቹ በአናሳ ብሄር አንገዛም ከሚሉት የኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል።

የሀረሪ ክልል የጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ አህመድ በክልሉ ከሚካሄደው የሙስሊሞች ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ሲነሱ፣ የገቢዎች ሀላፊ የሆኑት አቶ አህመድ፣ የሚሊሺያ ሀላፊው አቶ ኡስማን፣ እንዲሁም የየረር ቀበሌ አፈ ጉባኤ የሆኑት አቶ ሙመድ ድረም በአናሳ ቡድን አንገዛም የሚለውን ቡድን ይመራሉ በሚል እንዲነሱ ተድርጓል። በክልሉ የሚታየው ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ነው ምንጫችን የገለጹት።

No comments:

Post a Comment