Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, November 29, 2012

ሰበር ዜና፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮችን አስተናገደች፣

Ethiopian Plarliament Playing toys
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የተለያዩ ድህረገጾች ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ሦሥት ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮች እንደሚኖራቸውና ሃገሪቱንም በቡድን እንደሚመሩዋት መገለጹ የሚታወቅ ነው። ከዚያም ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ሁለት ተጨማሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮችን እና አንድ ወሳኝና ቁልፍ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱን ቦታ ለህወሓት በማስረከብ አጸድቀዋል። 


ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ የቀረበውን የካቢኔ አባላት ሹመት ባፀደቀበት ወቅት እንደተገለፀው የካቢኔ ጉዳዮች በማሕበራዊ፣ በመልካም አስተዳደር እና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ተከፋፍሎ ሹመቱ መካሔዱን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል።

በዚህ መሠረት የኦህዴዱ አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስትር አስተባባሪና ሲቭል ሰርቪስ ሚኒስቴር፤ሃገሪቱ ነፃ ሚዲያ እና እውነተኛ የመረጃ ፍሰት እንዳታገኝ በማፈን ሌት ከቀን ጠንክረው ይባትኑ የነበሩት የህወሓቱ ምክትል ሊቀመንብር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ማዕረግ፤ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኒዎሎጂ ሚኒስትር፤ የህወሓቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፤

ከብአድን ተጠባባቂ የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ከበደ ጫኔ የንግድ ሚኒስትርና ከጉራጌ ብሔረሰብ የሆኑት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ ደግሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በመሆን ከተሾሙ በሗላ አዲሶቹ ተሿሚዎች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካይነት ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ ታይተዋል።

ኦህዴድ ቁልፍ የስልጣን ቦታ አጥቷል በሚል ከፍተኛ ከሆነ ብጥብጥ ውስጥ ገብት የነበረ ቢሆንም የአቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዕረግ መሾም ጉዳዩን ለማብረድ ቢሆንም አሁንም ቁልፍ የሚኒስትር ስልጣኖች በህወሓት እጅ መቀመጣቸው  ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ እና አድሎዓዊው ሹመት አሁንም እንዳለ ነው የሚሉ ብዙዎች ሲሆኑ፤ ይልቁንስ ሳንዘናጋ ተባብረን ይህን የገማ የሚነደኞች ጥርቅም ለማስወገድ መጣር አለብን ሲሉ ያሳስባሉ።    

No comments:

Post a Comment