Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, September 24, 2012

በኮሪያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የባጀት ጥረት ገጠመው

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበጀት ዕጥረት ምክንያት እኤአ 2001  በሩን ዘግቶ ከተመለሰ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በ2012  ቢከፈትም ገና ስራውን ከጀመረ 3 ወራትን ሳያስቆጥር ዳግመኛ የበጀት እጥረት እንደገጠመውና ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እንዳጣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የውስጥ ሰራተኛ አስታወቁ።


ሰራተኛው ለኢሳት በላኩት መልእክት ኢምባሲው በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ይገኛል። ለሰራተኞቹ ሊጠበቁ የሚገባቸው ጥቅማጥቅሞች ፈፅሞ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጉዳዮች ሆነዋል በማለት ግለሰቡ ገልፀዋል።

በተለይም  ሰራተኞች የጤና ኢንሹራንስ የለንም፣ የጡረታ አበል አይከፈልልንም፣ የአደጋ ጊዜ ኢንሹራንስ የለንም፣ የአገልግሎት አበል አልተከበረልንም፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ አይከፈለንምና የተደራረበ የስራ ጫና አለብን በማለት ቢያሳውቁም መልስ አላገኙም።

በአንድ በኩል በበጀት እጥረት ምክንያት ለሰራተኛ የሚከፈል ደመወዝ እንዲስተጓጎል እና አስፈላጊ የሰው ሃይል ቅጥር እንዳይደረግ ቢደርግም በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ የተጋነነና  ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለኮርያ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ተደጋጋሚ ግብዣ እንደሚደረግ የውስጥ ሰራተኛው ቅሬታቸውን ለኢሳት ገልጠዋል።

No comments:

Post a Comment