Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, September 24, 2012

በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት በሻርጃህ ከተማ 36 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:- ኢምሬት ኒውስ እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ በሻርጃህ ፖሊስ የታሠሩት ከስፖንሰሮቻቸው ጠፍተው በመገኘታቸው ነው።

ኢትዮጵያውያኑ  በኢምሬት -አረብ ቪላ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃ ከደረሰው በሁዋላ በቁጥጥር ሥር  እንዳዋላቸው የገለጸው የሻርጃህ ፖሊስ፤ በህገ-ወጥ መንገድ በሥራ ተሰማርተው እንደነበር አመልክቷል።


ጉዳያቸው ወደ አቃቤ ህግ ተልኮ በሁሉም ላይ ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ፖሊስ አስታውቋል። በተመሣሳይ መንገድ የተሰማሩ ስደተኞች ካሉ ህዝቡ መረጃ እንዲሰጥ የሻርጃህ ፖሊስ በሚዲያዎች ጥሪ አቅርቧል።

ባለፈው ዓመት በሳዑዲ ዐረቢያ- ሪያድ ውስጥ የገናን በ ዓል ምክንያት በማድረግ ተሰባስበው ሲጸልዩ የነበሩ 35 ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ፖሊስ ለወራት ታስረው ከፍ ያለ ስቃይና መከራ ካሳለፉ በሁዋላ በ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment