Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, September 9, 2012

የኦጋዴን በህራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ

ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ አነሳሽነት በኢህአዴግ መራሹ መንግስትና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር መካከል እኤአ ከመስከረም 6 እስከ 7፣ 2012 ባሉት ቀናት ውስጥ ድርድር ተካሂዷል።

ውይይቱ የተመራው በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በሆኑት አቶ አብዱራህማን ማሀዲ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሀሰን ፈርጌሳ መካከል ነው።


ውይይቱን የመሩት ደግሞ የኬንያው የእርሻ ሚኒስትር እና የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ ናቸው።
ሁለቱም ወገኖች በድርደሩ ሞዳሊቲ ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒሰትሩ አቶ በረከት ስምኦን ገልጠዋል።

ኢሳት ከወራት በፊት በመንግስትና በኦብነግ መካከል ድርድር እንደሚጀመር የኦብነግን አመራሮች በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። በወቅቱ የኦብነግ አመራሮች ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ቀድም ብሎ ተይዞ የነበረው ድርድር መልኩን ሊለውጥ ይችላል በማለት ተናግረው ነበር ።

የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ ድርድሩን የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ እንደተጠቀመበት ይገልጣሉ።

No comments:

Post a Comment