Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, July 11, 2012

ግራ የተጋባው ፓርላማ ነገ ለልዩ ስብሰባ ተጠራ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመዝጊያው ጊዜ እስከዛሬ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የተራዘመው ፓርላማ ፣ ነገ ረቡእ ለልዩ ስብሰባ ተጠርቷል። በነገው ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይገኙ እንደሆን ለምንጫችን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ፣ “እስካሁን ድረስ ይገኛሉ የሚል ፍንጭ አለመሰማቱን፣ ይሁን እንጅ ይገኛሉ ብለው እንደማያስቡ” ተናግረዋል።

በፓርላማው አሰራር መሰረት አቶ መለስ በተገኙበት የሚቀጥለው አመት በጀት ለፓርላማው ተልኮ ከጸደቀ በሁዋላ፣ ፓርላማው ለእረፍት ይዘጋል። በነገው እለት ከሚቀርቡት አጀንዳዎች መካከል የበጀት ማጽደቅና የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ተሳትፎ የሚጠቁሙ አጀንዳዎች አልተካተቱም። 


በዚህም የተነሳ አሁንም በጀቱ መቼ እንደሚጸድቅ፣ አቶ መለስ መቼ ፓርላማ ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር እንደሚያድረጉ የፓርላማ አባላት አያውቁም። አንዳንድ የፓርላማ አባላት ለአፈጉባኤው ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ” ጥሪ ተጠባበቁ” የሚል መልስ ብቻ ማግኘታቸውን ለዘጋቢያችን ገልጠዋል።

ትናንት የአቶ መለስ ዜናዊን የጤና ሁኔታ በማስመልከት በሰራነው ዘገባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ በደቡብ ሱዳን 1ኛ አመት የነጻነት በአል ላይ ይገኛሉ ተብሎ ቢጠበቀም፣ በእርሳቸው ቦታ ምክትላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ፎርቹን ጋዜጣ “ፋይን ላይን” በሚለው አምዱ አቶ መለስን የጠየና ሁኔታ ዘገባ ይዞ ወጥቷል።

 ጋዜጣው አቶ መለስ ዜናዊ ያለፈውን ሳምንት ውጭ አገር ሄደው መታከማቸውንና አገር ውስጥ አለመኖራቸውን ገልጧል፡፤ እርሳቸው ወደ ለንደን እና ሌሎች አገሮች ተጉዘው የታከሙበትን ወጪ የገንዘብ ሚኒስቴር ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስተላላፉን፣ ሌሎች መስሪያ ቤቶችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ህክምና ያወጡትን ወጪ እንዲያሳውቁ የተጠየቀበት ሰርኩላር ደብዳቤ እንዲታደግ መደረጉን ዘግቧል።

ፎርቹን ” የአቶ መለስ የቅርብ ሰዎች አቶ መለስ ክብደት የቀነሱት በቅርቡ የምግብ መቀነስ ወይም ዳይት በመጀመራቸው ነው” የሚል መልስ እንደሚሰጡ፣ የዲፐሎማቲክ ምንጮች በበኩላቸው ” ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ህክምናቸውን ጨርሰው በሙሉ ጤንነት ባለፈው ቅዳሜ ወደ አገር ውስጥ መግባታቸውን መናገራቸውን ” ጽፏል።

ጋዜጣው ህዝብ እየተነጋጋረ፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች ወገኖችም ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተሉት በመሆኑ መንግስት ወሬው ከቁጥጥር ውጭ ሳይወጣ፣ የመንግስት ፕሮፓጋንዲስቶች” አንድ ነገር እንዲሉ መክሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀናት በፊት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ 80 አውቶብሶች፣ እንዲሁም ከባድ መሳሪዎችን የጫኑ በርካታ ሎቤድ መኪኖች ወደ ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል አቅንተዋል። በሰሜኑ አካባቢ ወታደራዊ ጥበቃውን ለማጠንከር ለምን እንደተፈለገ የታወቀ ነገር የለም።

Source: Ethsat news

No comments:

Post a Comment