Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, June 10, 2012

አልሸባብ ፕሬዚዳንት ኦባማንና ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩዋን ለመግደል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ሁሉ እንደሚከፍል አስታወቀ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አልሸባብ ፕሬዚዳንት ኦባማንና ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩዋን ለመግደል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ሁሉ ገንዘብ እንደሚከፍል አስታወቀ የሶማሊያ ታጣቂ ሀይል ይህን መልስ የሰጠው የባራክ ኦባማ አስተዳዳር የአልሸባብ መሪዎች ያሉበትን ለጠቆመ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጥ ማስታወቁን ተከትሎ ነው።

የአልሸባብ የቆዩ መሪ የሆኑት ሼክ ሾንጎሌ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንት ኦባን ለመግደል የሚያስችል በቂ መረጃ ለሚያመጣ ሰው 10 ግመሎችን ይሸልማሉ፤ በአንጻሩ ሂላር ክሊንተንን በተመለከተ ለሚመጣ መረጃ ደግሞ 10 ሴትና 10 አውራዶሮውችን እንደሚሰጥ አስታውቋል። የፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር የአልሸባብ መሪዎችን ለሚጠቁሙ 33 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ማስታወቁ ይታወሳል።

ሼክ ሸንጎሌ  ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎችን ማምለጣቸውን ፕሬዚዳንት ቡሽን እንደተዋጉት ሁሉ ኦባማንም እንደሚዋጉ ገልጠው፣ አሜሪካ መንግስት አቀረብኩ ለሚለው አዲሰ እቅድም አሜሪካዊያንን በመጥለፍ እንደሚበቀል ዝቷል።

አልሸባብ ከአልቃይዳ ጋር በይፋ መቃላቀሉን ካስታወቀበት ጊዜ ጀምሮ እየተዳከመ መምጣቱ ይነገራል። ምንም እንኳ ታጣቂ ሀይሉ አሁንም ሰፊ የሶማሊያን ግዛት ተቆጣጥሮ የያዘ ቢሆን፣ ከአፍሪካ ህብረት ጦር እየደረሰበት ባለው ጥቃት፣ ቀሪ ይዞታዎችን ሊያጣ ይችላል የሚሉ ግምቶች እየተሰነዘሩ ነው።

No comments:

Post a Comment