Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, June 11, 2012

በሰሜን ጎንደር የሚገኘው የመኢአድ ጽህፈት ቤት አባሎቻቸው በገፍ መታሰራቸውን ገለጠ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ጽህፈት ቤቱ ለኢሳት በላከው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ በዜጎች ላይ የሚደርሰው እስራት፣ ግርፋት፣ ስደትና ረሀብ ከልክ አልፎአል ብሎአል።

በሰሜን ጎንደር በጭልጋ ወረዳ የመኢአድ ም/በት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መለሰ አስሬ ግንቦት23 ከቀኑ በ10 ሰአት ከ10 በላይ በታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች በሀይል ተወስደው የደረሱበት አለመታወቁን፣ የጃናሞራ ወረዳ መኢአድ ም/ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ስለሺ ጥጋቤነህ ግንቦት 23 ከቀኑ በ10 ሰአት ደባርቅ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፌደራል ፖሊሶች በሀይል መወሰዱና የደረሰበት አለመታወቁን ገልጧል።

በማግስቱ ደግሞ የሰሜን ጎንደር መኢአድ ጽህፈት ቤት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ታድሎ ተፈራ በፌደራል ፖሊሶች ተወሰደው የደረሱበት አለማታወቁን እንዲሁም አቶ ካሳሁን በክረጽዮን ከሚኖሩበት የወቅን ከተማ ተወስደው መደብደባቸውን፣ መታሰራቸውን፣ ቤታቸው መዘረፉንና ሀብት ንብረታቸውን መቀማታቸውን ድርጅቱ ገልጧል።

ኢሳት የሰዎችን ታፍኖ መወሰድ በተመለከተ ባለፈው ሳምንት ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። ታፍነው የተወዱት ሰዎች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የታወቀ ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment