Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, May 11, 2012

አቶ ክፍሌ ስንሻው በማረሚያ ቤት አረፉ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በሀገር ክህደትና ህገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ አሲረዋል ተብለው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው በቃልቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክፍሌ ስንሻው በትላንትናው እለት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

በዛሬው እለት አስከሬናቸው ከፖሊስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ ሚንሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ሄዷል ያሉን ምንጮቻችን፣  በማረሚያ ቤት በቂ ህክምና እና መድሃኒት እንዳያገኙ ሳንካ ሲደረግባቸው ህመማቸው በመባባሱ በመጨረሻው ፖሊስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው አልፏል ብለዋል፡፡ 

ቤተሰቦቻቸው አቶ ክፍሌ እንደሻውን ወደ ጎጃም ሞጣ ወስደው ለመቅበር ቢፈልጉም ማረሚያ ቤቱ ቤተሰቦች ስለመሆናችሁ ከቀበሌ የድጋፍ ደብዳቢ እንዲያመጡ በማዘዙ ዘመዶቻቸውን  በመጉላላት ላይ መሆኑ ታውቋል። አቶ ክፍሌ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሙከራ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ ከፍተና የሆነ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል።

በሌላ በኩል ደግሞ የመለስ መንግስት እነ ጄኔራል ተፈራ ይቀርታ እንዲጠይቁ የተለመዱ ሽማግሌዎችን ወደ ቃሊቲ መላኩ ታውቋል። የሽማግሌዎቹ ጥረት በምን ደረጃ ላይ መሆኑን ለማወቅ ባይችልም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የአማራ ተወላጅ  የጦር መኮንኖችን በመፍታት መንግስት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብአዴንን ጨምሮ ከአማራው ህዝብ እየተነሳበት ያለውን ተቃውሞ ለማብረድ ሊሞክር ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ።



No comments:

Post a Comment