Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, May 8, 2012

ከሁመራ ከ50 በላይ ሰዎች በድጋሚ ታፍነው ተወሰዱ -አንድ ሰው ሞቷል

 Fetehe.com
በምዕራብ ትግራይ ክልል በቃፍታ ሁመራት ወረዳ ተከዜ ወንዝ ዳርቻ ‹‹ከርቸሊት›› ከምትባል አካባቢ ከትናንት በስትያ ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸውን፣ አንድ ሰው መሞቱንና አራት ሰዎች ከተያዙ በኃላ ማምለጣቸውን የአካባቢው ምንጮች ለፍትሕ ገለፁ።

በአካባቢው በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ከነበሩት በርካታ ሰዎች መካከል ከትናንት በስትያ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ በግምት 58 የሚሆኑ ሰዎች ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል። በወቅቱም የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ የጠቀሱት ምንጮቻችን፣ አቶ ገ/መድህን ተክላይና አቶ ገ/መድህን ገ/ኢየሱስ የተባሉ ግለሰቦች ከተያዙ በኃላ ሮጠው ማምለጥ እንደቻሉ ተናግረዋል።

 ፍትሕም አቶ ገ/መድህን ተክላይን በስልክ ለማነጋገር ችላ ነበር፡ ፡ እንደተባለው ከአፈናው ሮጠው ማምለጣቸውን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን በድርጊቱም አንድ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይልን በተጠርጣሪነት ጠቁመዋል። መንግስት ስለጉዳይ ስላለው መረጃ ለመጠየቅ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ወደሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ  ብንደውልም ስልካቸው ስለማይነሳ የመንግስትን ምላሽ ማካተት አልቻልንም።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሚያዚያ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. በዚሁ አካባቢ ‹‹ሀገረ ሰላም›› በሚባል አዲስ ሰፈር ከ140 በላይ ነዋሪዎች ባልታወቁ የታጠቁ ሃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ከጉራፈርዳ ወረዳ ‹‹አረን ዳገት›› ከሚባለው አካባቢ የተፈናቀሉ 47 አባወራዎች ሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለሰዓታት ካረፉ በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ደብረብርሃን መጓዛቸው ታወቀ።

ከስድስት ዓመታት በላይ መኖሪያቸውን በዞኑ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ በዞኑ በሌሎች አካባቢዎች ሲካሄድ የነበረው የማፈናቀል ተግባር ቀደም ባሉት ጊዜያት እንዳልነበረ ገልፀው፣ ነገር ግን ከሚያዚያ 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹ከዞኑ ጥላችሁ ውጡ›› ተብለው መገደዳቸውን ለፍትህ ገልጸዋል፡፡

‹‹ለምን ብለን በመጠየቃችን ታስረን ተደብድበናል›› የሚሉት ተፈናቃዮቹ  ‹ቤተሰቦቻችንን ወደከተማ በመሸሸግ እኛ እዛው ብንቆይም ከያለንበት በሦስት ቀናት ውስጥ ለቀን እንድንወጣና በአካባቢው ያፈራነውን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ጊዜ ሳናገኝ እንድንባረር አስገድደውናል›› ብለዋል፡፡

የትውልድ አካባቢያቸው ሰሜን ሸዋ መሆኑን የሚናገሩት  እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን በመሄድ የዞኑ አስተዳደሩ በሌላ ቦታ እንዲያሰፋራቸው ለመጠየቅ ከላይ በተጠቀሰው እለት ተጉዘዋል፡፡

No comments:

Post a Comment