Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, April 6, 2012

አቶ መለስ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች ቃሊቲ እየተመላለሱ ነው

 የኢሳት አማርኛ ዜና »  መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

የአቶ መለስ መንግሥት የወከላቸው ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ የፖለቲካ እሥረኛ የሆኑ ፍርደኛ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን  ይቅርታ ለማስጠየቅ  የማግባባት ሙከራ ማድረግ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የፍትህ ሚኒስቴር  ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የተወከሉ ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት እየተመላለሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሊቀመንበርን አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚሃብሄርን፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል  ዋና አዘጋጅ የነበረውን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን፣ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛን መምህርት ርዕዮት ዓለሙን  እና የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ አባል የነበረችውን ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌን በተደጋጋሚ በማነጋገር፤ መንግሥት በይቅርታ ሊፈታቸው እንደተዘጋጀ አስታውቀዋቸዋል፡፡ በዚህ መሠረትም ከርዕዮት ዓለሙ በስተቀር ሁሉም የይቅርታ ፎርሙን ሞልተው ለፍትህ ሚኒሥቴር የይቅርታ ቦርድ መላካቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በይቅርታ ፎርሙ ላይ ለእያንዳንዳቸው ፍርደኞቹ በእውነት ተጸጽተው ስለመፈረማቸው ዋቢ የሚሆኑና ከቤተሰብና ከቅርብ ጓደኛ የተውጣጡ  ሦስት ሦስት ሰዎች  የድጋፍ ቅጽ መሙላታቸውም ተገልጿል።

ይሁንና ማረሚያ ቤቱ ከወይዘሮ ሂሩት በስተቀር  የሌሎቹን  የድጋፍ ቅጽ  ለፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ባለማስገባቱ፤ ጉዳያቸው መታየት እንዳልጀመረ እና አንድ ቢሮ ውስጥ ታግቶ እንደሚገኝ ምንጮቹ  ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእሥር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት እርዮት ዓለሙ በማዕከላዊ እስር ቤት ሆን ተብሎ በቀዝቃዛ ሲሚንቶ ላይ እንድትተኛ በመደረጉ በእግሯቿ ላይ ካጋጠማት የቁርጥማት በሽታ በተጨማሪ በጡቷ ላይም ህመም እየተሰማት መሆኑን ፤ የማረሚያ ቤት ምንጮች ተናግረዋል። ከሁለት ሣምንት በፊት ጀምሮ ርዕዮት በህመም እየተሰቃየች መሆኑን የገለጹት ምንጮቹ፤ ህክምና ታገኝ ዘንድ ለማረሚያ ቤቱ ያቀረበችው ጥያቄም፦” ሴት አጃቢ ፖሊስ የለም”በሚል ምላሽ ሳይሳካ መቆየቱን ተናግረዋል።
ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ መጋቢት 25 ቀን ማረሚያ ቤቱ ፦”ሴት አጃቢ ፖሊስ አግኝቻለሁ” በማለቱ ርዕዮት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስዳ ምርመራ እንደተደረገላት ምንጮቹ አመልክተዋል።

No comments:

Post a Comment