Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 22, 2012

አቶ መለስ ዜናዊ ሞተውም በከፍተኛ እጀባ እተጠበቁ ነው

ኢሳት ዜና:-አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለተቀበሩት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ መለስ ዜናዊ  ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታተም ቢከለከልም  “ኦን ላይን” ጋዜጣ በመሆን  በኢንተርኔት ስርጭቱን የቀጠለው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፤ አቶ መለስ ከተቀበሩ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሮች የተቆለፉ ሲሆን፤ መቃብራቸው በተለየ ኃይል ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት ነው፡፡

Sunday, September 16, 2012

ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!!

ህወሓትና ስዩም መስፍን በኢህአዴግ ምክር ቤት ድምጽ ተነፈጉ! Source: www.goolgule.com

የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም።

በሐሰት ወሬ ሕዝብን ለአመፅ አነሳሳ የተባለ ግለሰብ በአንድ ዓመት እስራት ተቀጣ

By reporter: የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ የወንጀል ችሎት፣ በመንግሥት ላይ ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ሕዝብን በሐሰት ወሬ አነሳስቷል የተባለውን ግለሰብ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጠ::

ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦነግና ለኤርትራ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተከሰሱ

አገርን አደጋ ላይ የሚጥል ሚስጥር አሳልፈው መስጠታቸው ተጠቁሟል::
በሚስጥር የሚጠበቁና በሕዝብ በይፋ የማይታወቁ ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና ለኤርትራ የደኅንነት ሠራተኞች አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሁለት መከላከያ ሠራዊት አባላትና ሁለት ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው:: 

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ኢሳት ዜና:-ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን የያዘውና180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጉባዔ በሞት በተለዩት የግንባሩ ለቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ የብአዴኑን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል አድርጎ መምረጡን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡

ጉባዔው በዛሬው ውሎው በገጉት ሲጠበቅ የነበረውን የግንባሩን ሊመንበር ምርጫ ያከናወነ ሲሆን አዲሱ ተመራጭ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ምንጫችን እንዳለው በኢህአዴግ የእስከዛሬ ልምድ ግንባሩ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ጠቁሞ ይህ ግን ተለምዶያዊ አሰራር እንጂ ሊቀመንበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል የሚል በግንባሩ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ የመንግስት ሕግ አለመኖሩን አስታውሶአል፡፡በዚህ መሰረት ግንባሩ ከሊቀመንበሩ ከአቶ ኃይለማርያም ውጪም ሊመርጥ የሚችልበት ዕድል ዝግ አለመሆኑን ያስታወሰው ምንጫችን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን የአቶ ኃይለማርያም መሾም አጠራጣሪ አለመሆኑን አመልክቶአል፡፡

የፋና ራዲዮ ዘገባ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን አስቆጣ

ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ኢንዶውመንት ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የሚታወቀውና ራሱን  “የግል ራዲዮ ጣቢያ” በማለት የሚጠራው ራዲዮ ፋና “ኢትዮፒካሊንክ” በሚል ርእስ በኤፍ ኤም የሚያሰራጨው ፕሮግራም ከአቶ መለስ ዜናዊ፤ ዜና ዕረፍት ዘገባ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ቁጣ ታገደ፡፡

አቶ መለስ፤ ዜና ዕረፍታቸው በይፋ በመንግስት ከተነገረ በኃላ እስከቀብር ዕለት ድረስ የጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሞች ታጥፈው የነበረ ቢሆንም የኢትዮፒካሊንክ አዘጋጆች ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም ከአቶ መለስ ሕልፈተ ሕይወት ጋር በተያያዘ ልዩ ፕሮግራም እንዳላቸው በመግለጽ ጣቢያውን አስፈቅደው ያስተላለፉት ፕሮግራም በተለይ  የአቶ መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን አስቆጥቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ

ኢሳት ዜና:-የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ወደ ኦጋዴ ክልል በመግባት በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረጽ ሲሞክሩ በታጣቂዎች ተይዘው ላለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ከታሰሩ በሁዋላ ሰሞኑን የተለቀቁት ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ እስር ቤት በእስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስከፊ መሆኑን ገልጸዋል።

Friday, September 14, 2012

“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡

ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ?

Thursday, September 13, 2012

ESAT New year Message Dr Birhanu Nega

Dr. Berhanu Nega was elected as mayor of Addis Ababa, Ethiopia in the Ethiopian general elections, 2005. He is a founding chairman of the Rainbow Ethiopia: Movement for Democracy and Social Justice and a Deputy Chairman of Coalition for Unity and Democracy (CUD), for whom he served as chief election campaign strategist. Dr. Berhanu is also the co-founder of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy, an opposition party and he is currently a chairman of the party.  see the video Speech.

አና ጎሜዝ መለስ የሞቱት በሃምሌ መሆኑን አጋለጡ

(Sept. 12) የአውሮጳ ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጎሜዝ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን የሞቱት በሃምሌ (July) ወር መሆኑን አጋልጠው አንባገኑ የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጥር ይዞ ጭቆናውን ለመቀጠል ሲሞክር እና ይፋዊ የስልጣን ሽግግር አለማድረጉን የአውሮፓ ፓርላማ በቸልታ መመልከቱ አግባብ አለሞሆኑን በቅርቡ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጨቋኝ አገዛዝ እንዲቀጥል የማድረግ ሙከራ ለማስተካከል አለመጣሩ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የጋራ የውጭና የደህንነት ስትራቴጂክ ጥቅም ጋር ይጋጫል ሲሉ ተናገሩ።