Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, July 7, 2013

የሰብአዊ መብት ረገጣንና ኢትዮጲያዊውያንን በገዛ ሀገራቸው የዜግነት መብት ያሳጣውን ዘረኛ ሥርዓት በጽኑ እየታገልን አባይም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሚጠቅም መልኩ ይገደባል።


አገራችን በዓባይና በመጋቢ ወንዞች ላይ ግድብ ለመሥራት ሙከራ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። 1959 / (..) በግብፅና በሱዳን መሃል በተናጠል የተደረገውን ስምምነት በመቃወም አስር ሚሊዮን ዶላር በመመደብና በአሜሪካ ሙያተኞች አማካኝነት አያሌ ግድቦችን ለመገንባትና የውሃ ሃብቷን ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም 1964 / (..) ጥናቶችን ማጠናቀቋን መጥቀስ ይቻላል።

የዚህን ዓይነት ብሔራዊ ጉዳይ ለማስፈጸም ወያኔ ብቻውን አመራሩን ጨብጦ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያለነውን ዜጎች በማስገደድም ይሁን በማታለል ገንዘባችንን ለመሰብሰብ ሲነሳሳ እኛም እንደ ዜጋ ይህ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብቱ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠብቆና ተከብሮ በአገሩ ኮርቶ በፈቃደኝነትና በደስታ የሚሳተፍበት እንዲሆን እንፈልጋለን።

በእውነት ወያኔ ይህንን ብሔራዊ አጀንዳ በዚህ ወቅት ያነሳው ለኢትዮጵያዊያን አስቦ ከሆነ በሃይማኖታዊ  እምነትና በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ያሰራቸውን ወገኖቻችንን እንዲፈታና ከየቀያቸው ማሳደዱንም እንዲያቆም መጠየቅ ሰብአዊ መብታችንና ግዴታችንም ነው። የእኛ ጥያቄ የመብት የአንድነትና የፍትህ ጥያቄ ሆኖ አባይንም የመጠቀም መብት የግብፅና የሱዳን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ጭምር መሆኑን በዚሁ ልናሰምርበት እንወዳለን። የእኛም ሚና ገንዘብ ከማዋጣት ያለፈ ነው ብለን ስለምናምን ለዛሬው ስለ ህዳሴው ግድብና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉንን ነጥቦች እንደሚከተለው እናቀርባለን።

የወያኔ የአባይ ፖለቲካዊ ሰሌትናየህዳሴው ግድብ”.ለኢትዮጲያ ህዝብ
እንዲሁም ለተፋሰሱ ግርጌ ሃገራት ያለው ፋይዳ፡-

ፕሮጀክቱ እንደ ተአምር በሚወራው የአምስት ዓመቱየልማትና ትራንስፎርሜሽን”. እቅድ ውስጥ ያልተካተተ ሲሆን እቅዱ የመጣውባለራዕዩ መሪ”. በሰሜን አፍሪካ የተቀጣጠለው የጸረ አምባጋነን ዓመጽ እሳቸውንም እንዳይጠርጋቸው በመስጋትና የኢትዮጵያ ህዝብ በአባይ ላይ ያለውን ጥልቅ ብሄራዊ የቁጭት ሰሜት በማጤን የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ እንዳስፈላጊነቱ ለመዘወር እንደሚቻል በህወሃቶች ስለታመነበትና የህዝብን ትኩረት በማስቀየር ጥቂት እድሜ ለመግዛት ታስቦ ነው። ወያኔ በዕብሪት መንፈስ ግድቡን የግል ጉዳዩ ብቻ አድርጎ በመምራት በሃገራችን ሃብትና ሞራል ርካሽ የፖለቲካ ጥቅምም ለመግዛት አስቦ በድንገት ያመጣው የፖለቲካ ቁማር ነው። ለዚህም ምስክሩ በየሀገሩ የአባይ ቦንድ ለመሸጥ በግንባር ቀደምትነት የሚሯሯጡትና እራሳቸውን የግድቡ ባለቤት አድርገው የሚቀርቡት ግለሰቦች የወያኔ ሰዎች መሆናቸው ነው።

የህዳሴ ግድብ ለግንባታ ከተመረጠበት ቦታ እስከ ታቀደለት አላማ ድረስ ለኢትዮጵያ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ በተለይ ለሱዳን የሚሰጠው ጥቅም እጅግ የላቀ ነው። ለማስረጃ ሁለት ነገሮችን መጥቀስ ይበቃል።

1) የሱዳን በመስኖ የመጠቀም ሀቅም እሁን ከአለው የሶስት ወር ጊዜ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ አስራ ሁለት ወር ከፍ ያደርገዋል። በአንጻሩ ግን ኢትዮጵያ ሰማንያ ቢሊዮን ብር ውጭ ግድቡን ሰርታ አንድ ስኩየር ሜትር መሬት እንኳን በመስኖ ማልማት አትችልም።

2) ይህ ግድብ በኢትዮጵያ በኩል ታቅዶ እየተገነባ ያለው ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ሃይል ብቻ በማምንጨት ለጎረበት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ብቻ ነው። እስከአሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለዉን የመብራትም ሆነ የሀይል እጥረት በተወሰነ መልኩ ለማቃለል እንኳን እቅድ አልተያዘለትም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ በብሄራው ስሜትና አንዳንዴም በፍራቻ እንዲሁም በግዴታ ከሌለው ኪሱ ሰማንያ ቢሊዮን አዋጦ ከሰራው ግድብ መብራት እንኳን ሳያገኝ ጎረቤት ሃገራት በተለይ ሱዳን በቅናሽ ከፍያ (በዶላር ስለሚከፍሉ ብቻ) ከህዳሴ ግድብ በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ሀይል ይንበሽበሻሉ። የግድቡ ውሃ ግን በኢትዮጵያ ለም መሬት ላይ ያርፋል። ውሃው የሚያርፍበት መሬት ስፋቱ ሲንጋፖር የምትባልን ሀገር ሁለት እጥፍ ይሆናል።

ሱዳን ግድቡ ድንበሯ አጠግብ በመሰራቱ ደስተዋን የገልጸችው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ነበር፤ ለዚህም ለዋቢነት የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተናገሩትን መጥቀስ ያስፈልጋል። እንዲህ ይነበባል፡-. “the dam will bring many benefits and blessings for us,” Informa_on Minister Ahmed Bilal Osman (Bloomberg June17, 2013). በነገራችን ላይ ለሱዳን ሰፊ ለም መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርሶ መሰጠቱ የቅርብ
ጊዜ ትዝታ ነው። እና መሬቱ አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በሰማንያ ቢሊዮን ብር ግድብ ሰርተን መስጠት አለብን ማለት ነው? ለየትኛው ውለታዋ ግብፅስ በእውነት ግድቡ እርሷን የሚጎዳ ከሆነ እስከ ወንዙ ጠለፍ ዜና ድረስ ለምን ዝምታን መረጠች? የአሁኑስ ተቃውሞዋ ጠንካራ ያልሆነበት ጥቅም ስላላት ነው ወይስ ስለማያዋጣት? ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብፅ በበለጠ በህዳሴ ግድብ ተጠቃሚ ናትን? መንግስት ስለህዳሴ ግድብ ሲያልም ይዞት የተነሳው ግድቡን በኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ ማጠናቀቅ እንደሚቻል አድርጎ ነው። እውነታው ግን ይህ እንደማይቻል ከመጀመሪያው መንግስት እንድሚያውቅ ነው። ለዚህም ማስረጃ አምባሳደር ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የተባሉ (ውስጥ አዋቂ ዲፕሎማት) ሪፖርተር ለተባለ የመንግስት ደጋፊ ጋዜጣ የሰጡት ቃለመጠየቅ መጥቀሱ በቂ ይሆናል። እንደሚከተለው ይነበባል። "ሪፖርተር፡- የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ብቻ መሸፈን ወይም ዳር ማድረስ ይቻላል? አምባሳደር ኃይሉ፡- አንችልም፡፡"

ታዲያ መንግስት ለምን ለህዝብ መዋሽት ፈለገ? ለምን በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ብቻ ይሰራል ይለናል? ስለዚህም ነው ይህ ግድብ ፍፁም የሃገሪቷን ሃቅም ያላገናዘበ፤ ከወዲሁ የተመደበ በጀት ስለሌልው በማንኛውም መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሁሉ ወደዚሁ ግድብ ስራ ስለሚሄድ ግድቡ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ቀውስ በመፍጠር ኢኮኖሚውን በበለጠ ያዳክማል የሚባለው። ይህንንም የአለም ባንክ ያረጋገጠው ጉዳይ ነው። ስለዚህም ጉዳይ የአለም ባንክ ርፖርትን ማየት ይቻላል።

ከኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር መካከል በምግብ እራስን አለመቻልና ሥራ አጥነት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ መንግስትም ማተኮርና ቅድሚያ መስጠት ያለበት የመስኖ እርሻን ማስፋፋትና የግብርና ምርትን ማሳደግ ብሎም ለዜጎቹ የስራ እድል መፍጠር ነው። ይህ የህዳሴ ግድብ ሰማንያ ቢሊዮን ብር የሚፈስበት ቢሆንም እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች በመፍታት ረገድ እዚህ ግባ የሚባል አስትዋኦ አያደርግም። ለመስኖ እርሻ አይውልም፤ ከሚፈስበት ገንዘብ አኳያ በጊዜዊነት በግድቡ ግንባታ ወቅት ከሚሰማሩ ሰራተኞች በስተቅር ይህ ነው ይሚባል የስራ እድልም አይከፍትም።

የህዳሴ ግድብ አቀንቃኞችና ሙሰና፡-

በየዓመቱ ጠቅላይ ኦዲተሩ በሚያቀርባቸው የኦዲት ሪፖርቶች እንደሚታየው በርካታ ቢሊዮን ብር በመንግስት ባለስልጣናት በሰራዊቱ አዛዦች በማን አለብኝነት ያለማቋረጥ እየተመዘበረ መሆኑን ያሳያል። 2011 . Global Financial Integrity ሪፖርት እንዳመለከተው 2000 -2009 . (..) ባለው ጊዜ ውስጥ 11.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ወጥቷል (ይህ ገንዘብ 3 የአባይ አይነት ግድቦች መገንባት ያስችል ነበር)።በቅርቡ Celebrity Net Worth የተባለ ድረ ገጽ እንደዘገበው ከመጽሀፍት በቀር ቤሳ ቤስቲን የለኝም ሲሉ የነበሩትባለ ራዕዮ መሪ”. እንዲሁም ባለቤታቸው 4 ብር ነው የምንተዳደረው እያሉ የሚሳለቁብን ሰው በሰማቸው 3 ቢሊዮን ዶላር እንዳለ አሳውቆናል (ለማነጻጸር ስቴፈን ሀርፐር 5 ፣ ኦባማ 12.2 ሚሊዮን ዶላር ነው የሃብታቸው መጠን ግምት)

ለግድቡ እቃ ማቅረብን ጨምሮ የመንግስት ፕሮጀክቶች በሙሉ ማለት ይቻላል በአብዛኛው ያለ ግልጽ ጨረታ ለህወሃት ድርጅቶችና በዘመድ አዝማድ በዘረፋ ለተቋቋሙ ድርጀቶች የሚሰጥ ሲሆን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ምንም ያልነበራቸው የህወሃት አባላትና ዘመዶቻቸው ጥሩ የተባሉ የመኖሪያ ሰፈሮችን በመውረር ነባሮቹን በተለያየ ዘዴ በማፈናቀል ውድ በሆኑ የመኖሪያ ቤቶች የተድላ ህይወት እየኖሩ ነው። የሌላ ብሄር አባላት የሆኑ የግል ባለሃብቶችን በፈጠራ የታክስ ማጭበርበርና ሌሎች ወንጀሎች በመክሰስ እንዲሁም የመንግስት መዋቅሮችን በመጠቀም በተቀነባበረ የንግድ አሻጥር ከውድድር በማስወጣት ህወሃቶችና ጥቂት አጋፋሪዎቻቸው መንሰራፋታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እውን ወያኔ አባይን ለሃገር ጥቅም የመገደብ ሃሳብ ካለው ባለራዕዮ መሪ”.ስም ያለው ገንዘብ ብቻ የፕሮጀክቱን 71% ወጪ መሸፍን ይችላል። ከዚህ አንጻር ቀሪውን አንድ ከሳቸው አነስ ያለ ወያኔ ሊሽፍነው ይችላል ማለት ነው።

የህዳሴ ግድብና ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ፡-
እራሱ ወያኔ/ኢህአዴግ ያጸደቀውን ህገመንግስት በመጣስ ዜጎችን አሸማቆና አዋርዶ እያሸበረ ለመግዛት በማሰብ የራሱ የሰለላ ሀይሎች በተላያዮ የሃገሪቱ ክፍሎች ፈንጂዎችን በማፈንዳትና የበርካት ንጹሃን ዜጎችን ህይውት በመቅጠፍ የተውኑበትን የግፍ ድራማ መነሻ በማድረግየጸረ ሽበርተኛ ህግ”. አጽድቆ፤የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ ሀይማኖትን በነጻነት የመከተልና የመሳሰሉ መሰረታዊ መብቶችን በሃይል በመጣስ እንደ ርዕዮት አለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከር አህመድን ጨምሮ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻቸንን ከጠላት እንኳን በማይጠበቅ የጭካኔ ሰቆቃ እይፈጸመባቸው ረዥም የእስር ዘመን በመግፋት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሳያንስ እንደ አጋዚና ፌደራል ፖሊስ ያሉት የአፈናና የጭፍጨፋ መሳሪያዎቹ ባለ ሀይላቸው ያለምንም ማመንታት የጭካኔ በትራቸውን በህዝብ ላይ እንዲሳርፉ መብት ለመስጠት በማሰ እነዚህ ሀይሎች የጭፍጨፋ ተግባራቸውን በሚያካሂዱበት ወቅት በሚውስዷቸው ማናቸውም እርምጃዎች በህግ እንዳይጠየቁ የሚደነግግ የህግ ረቂቅጥርስ ለሌለው”.ፓርላማ አቅርቧል።

በሌላ በኩል የፍትህ ስርዓቱ ችሎታ ሳይኖራችው ነገር ግን ለአገዛዙ ባላቸው ፍጹም ታማኘነት ብቻ ተመልምለው የሃገሪቱን የከፍተኛ ትምህርት የጥራት ደረጃ በማያሟላውና በተለምዶ ድንጋይ ማምረቻ”. ተብሎ ከሚጠራው ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በኮታእየተመረቁ”. በሚወጡ ምንደኛ ካድሬዎች የተሞላ መሆኑ ለሥርአቱ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ከመሆን አላለፉም። እስካሁን ፍትህ ያላገኙ በመንግስት ባለሰልጣናት ትዕዛዝ በጸጥታ ሀይሎችና በሰራዊቱ በህዝብ ላይ የተፈጸሙ እና እይተፈጸሙ ካሉ ወንጀሎች በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል፦
  • በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በደቡብና በአፋር ክልል እንዲሁም በሌሎች የተለያዩ የሃገሪቱክፍሎች በወያኔ ወኪሎች ሆን ተብለው በተቀስቀሱ የዘር ግጭቶች የጠፋው ህይወትና የወደመው ንብረት፣
  • በጋምቤላ በአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ፣
  • በሱማሌ ክልል ለረዥም ጊዜ በመካሄ ላይ ያለው ጭፍጨፋና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዳውን ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዳያገኝ በመከልከል ሆን ብሎ በረሃብና በበሸታ የማሰቃየት ተግባር፣
  • በኦነግ አባልነት ስም በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ያልተቋረጠ ግድያ፣ እስር ሰቆቃ፣
  • በምርጫ 97 ድምጻችን ይከበር ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ፣
  • ·በጅማ፣ በደሴ እንዲሁም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የክርስትናና የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን ሆነ ተብሎ ለማጋጨት የተደረጉ ጭፍጨፋዎችና የተከበሩ የዕምነት ቦታዎችን የማቃጠል ወንጀሎች፣
  • ·በጉራፈርዳ በቤኒሻንጉል አካባቢ በሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር ማፅዳት ወንጀል፣
  • ለሀገራችን ምንም ፋይዳ ባልነበረውና ከፍተኛ የህዝብ ሃብት በባከነበት የኢትዮ -ኤሪትሪያ ጦርነት በወያኔ አዛዦች ወታደራዊ ዕውቀት ማነሰና ለሌላው ኢትዮጲያዊ ዜጋ ባላቸው ከፍተኛ ንቀት በአብዛኛው ከተቀረው የኢትዮጲያ ክፍል የመጡ ወደ 70 የሚገመቱ ወጣቶችን ያስፈጁበት ሁኔታ።
እንግዲህ ይህ ሁሉ ግፍ ፍትህ ባላገኘበት ሁኔታ ነው ሌላ ነገር አትጠይቁ ዝም ብላችሁ አፋችሁን ዘግታችሁ ለግድቡ ገንዘብ አዋጡ የምንባለው!

የህዳሴው ግድብና የህዝብ የሰልጣን ባለቤትነት፡-

ዲሞክራሲያዊ ምርጫ”. በሃገራችን ወያኔ ከራሱ ጋር ተወዳድሮ 99.6 ወደ 99.9% በማሸነፍ እድገት ያሳየበት በከፍተኛ የሃገር ሃብት የሚከወን አሰነዋሪ ድራማ ሆኗል። በሌላ በኩል ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የፓርቲ ልሳኖቻቸውን ለማሳተም፣ ሌሎች የቀን ተቀን ተግባራቶቻቸውን ለማከናወንና አባላቶቻቸውን ለመሰብሰብ አዳራሾችን ለመከራየት ቀርቶ አመራሮች ተሰባስበው ሆቴል ቤት እራት መብላት የማይቸሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።በብሄራዊ ሰም በተደራጀው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ካሉት 60 ጀነራሎች 58 ወያኔዎች ሲሆኑ ከጀነራል ማዕረግ በታች በየደረጃው ያለው የሰራዊቱ የስልጣን ዕርከን ጭምር በአብዛኛው በነሱ የተያዘ ነው። በእያንዳንዱን የሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶች በግልጽ ወይም በስውር ሰራዎችን የሚዘውሩትም የህወሃት ሰዎች ናችው።

ያለ እውቀት ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የወያኔን የሰልጣን ዘመን ለማራዘም ባላቸው ፋይዳ ላይ ተመርኩዘው በሚወጡ ሰንካላ ፖሊሲዎች ምክንያት ህዝቡ በኑሮ ውድነት፣ በድህነት፣ በበሽታና ሰራአጥነት ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ እይተሰቃየ ይገኛል። በዚሀም የተነሳ ዜጎች በገዛ አገራቸ የመኖር ተስፋቸው ተሟጦ በአስቸጋሪው ጉዞ ላይ በአስተላላፊዎች እንዲሁም በባዕድ አገር ቀጣሪዎች የሚደርሰውን ዘግናኝ ግፍና ሰቃይ እያይዩና እያሰሙ ስደትን በመምረጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለዱር አራዊትና ለባህር አሳ ቀለብ እንዲሁም በቁማቸው እየተበልቱ ጉበት፣ ኩላሊትና ልባቸው እየተቸበቸበ ይገኛል። አብዛኛው የኢትዮጲያ ገበሬ ለምነቱ በተሟጠጠ ኩርማን መሬት የአመት ቀለቡን ልማግኘት ሲታትር እጀግ ለምና ውሃ ገብ የሆነውን የሀገሪቱን መሬት ዜጎችን ያልምንም ካሳና ምትክ መሬት ከይዞታቸው በማፈናቀል ለባዕዳን ደሃው ገበሬ ለደካማው መሬቱ ከሚከፍለው ግብር ባነሰ ዋጋ ያለምንም ዋስትና ለመቶ አመት
እይተቸበቸበ ይገኛል።

ሕዝቡ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በገዛ ሀገሩ ባይተዋር ሆኖ የባለቤትነት ስሜት እንዳያድርበት ተደርጎ፤ ለአባይ ግድብ ገንዘብ አዋጡ ግን ሌላ ሰባዊም ሆነ ፖለቲካው ጥያቄ አታንሱ ማለት ሌላ ንቅት ነው።በአጠቃላይ አባይን ገድቦ ለኢትዮጵያ ጥቅም ማዋልን የሚቃወም ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። ነገር ግን የግድቡ እቅደና የሰራው አካሄድ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ፤ ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደለዉ፤ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ይልቅ በጊዜዊ ፖለቲካ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው። በተጨማሪም አጥቃላይ ሁኔታው ሲታይ፤ ሱዳን ድንበር ላይ መሆኑ፣ ለመስኖ እርሻ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለሱዳን አመቺ እንዲሆን ስለተደርገ ይህ ግድብ በኢትዮጵያ ገንዝብ ሳይሆን መሰራት ያለበት በበለጠ ተጠቃሚዋ በሱዳን ወጭ መሆን አለበት። ይህንም በተመለከተ እራሱ መለስ ዜናዊ እንዲህ ሲል በአንድ ወቅት ጠቅሶታል። "የዚህ ግድብ ወጭ መሸፈን የነበረበት ሰላሳ ፐርሰንት በሱዳን ሃያው ፐርሰንት ደግሞ በግብጽ ነበር።"

ይህም የሚያሳየው ሁለቱ ሃገሮች ምን የህል በዚህ ግድብ ተጥቃሚ እንደሚሆኑ ነው። ይህ እንግድህ በአደባባይ የተነገረው ነዉ። እዉነቱ ደግሞ ቢወጣ ከላይ ለመግልጽ እንደተሞከረው እዉነተኛዋ ተጠቃሚ ከኢትዮጵያም በላይ ሱዳን ናት። ታዲያ ኢትዮጵያ በምን አቅሟ ነው የሰማንያ ቢሊዮን ብር ግድብ ሰርታ ለሱዳን የምትለግሰው? ለዚህም ነው በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ፤ ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደለዉ፤ የፖለቲካ ቁማር ነው የምንለው። ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደሞከርነው የወያኔ የፖለቲካ መስመር፣ የዛሬና ትናንት ተግባራቸው፣ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፣ ስለዜጎች መብት መከበርና ስለጋራ እድገት፣ ስለ ብሔራዊ ክብርና ኩራት ያላቸዉ ንቀት ሳይታረም፣ የሕዝብን የመብት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳሉ ከላይ እስከታች በሙሰና እንደተዘፈቁ ነው አባይን የምንገድብበት ገንዘብ አምጡ የሚሉን።

የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ተገርሥሶ የኢትዮጲያ ህዝብ የሥልጣን
ባለቤትነት ይረጋገጣል አባይም ይገደባል!!!

1 comment:


  1. ሰላም, ፎቶዬን በ https://plus.google.com/u/0/109055934069608293906 ለመጠቀም የመጠቀም መብት ለማግኘት እየሞከርኩ ነው.

    ReplyDelete