Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, January 10, 2013

የአላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ

alamata
ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል በአለማጣ ወረዳ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች  ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ያሉት ፣ የወረዳው የቤት አፍራሽ ግብረሀይል አባላት በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል ያሉዋቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሄዱበት ወቅት ነው።

ተማሪዎች፣ ህጻናት ፣ አዋቂዎች ከጧቱ 3 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሹ ድረስ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን የገለጡ ሲሆን፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ የሚተላለፉ መኪኖች  መተላለፊያዎች ተዘግተውባቸው ውለዋል።


ቤቶችን ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ የወረዳው ባለስልጣናት የህዝቡን ቁጣ በመፍራት ስራቸውን ሳያከናውኑ ወደ መጡበት ተመልሰ ዋል።  ተማሪዎች “ቤታችን ፈርሶብን ትምህርት አንማርም” የሚል መፈክሮችን ሲያሰሙ ፣ ወላጆች ደግሞ በለቅሶ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል::  አንድ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ የወላጆቹ ቤት ፈርሶ መማር ስለማይችል፣ የመንግስትን ፖሊሲ ለመቃወም መውጣቱን ተናግሯል።

ከቀኑ 11 ተኩል በሁዋላ ከመቀሌ የመጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ህዝቡን እንዲበተን አድርገዋል።  ብዙ ሰዎች ተዘርረው መውደቃቸውን አይን እማኞች ገልጸዋል የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከ25 አመታት በፊት ጀምሮ የተሰሩ ቤቶች ህገወጥ ናቸው በሚል እንዲፈርሱ መንግስት አዟል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር አደረግነው ጥረት አልተሳካም። በአዲስ አበባ በተመሳሳይ መንገድ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል። አላማጣ ቀድሞ በአማራ ክልል በወሎ አውራጃ ስር ይገኝ ነበር። ህወሀት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር አካባቢው ወደ ትግራይ ክልል እንዲዞር ማድረጉ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment