Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, October 19, 2012

በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።


ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ  በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ነው። ጓደኛዋም ከጋብቻ ውጪ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ወንጀል ተከሶ በ እስር እንደሚገኝ< አመልክቷል። የ አንድ ቀን አራሷ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ሁለት እግሮቿ በሰንሰለት በመታሰራቸው፤ ህፃን ልጇን ሜሪያምን ማቀፍ ተስኗት መታየቷን ድረ-ገጹ አስነብቧል።

ኢትዮጵያዊቷ እናት ለፍርድ ቤት በሰጠችው ቃልም ከእስር ከተለቀቀች ከህፃኗ ጋር ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ተናግሯለች። የወህኒዎቹ ሃላፊዎች ግን አራሷ ኢትዮጵያዊት ከወህኒ የምትወጣው የ እስር ጊዜዋን ከጨረሰች በሁዋላ እንደሆነ ነው የተናገሩት። 

ህፃን ልጇን ይዛ መሄድ ትችላለች?ወይስ አትችልም? የሚለው ጉዳይም ለወደፊት በ ህግ የሚታይ መሆኑን ነው የገለፁት። ወደ መካከለኛው ምስራቅና አረብ አገራት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ደረጃ በደረሰበት ሰ ዓት የ ኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመታደግ ምንም እንቅስቃሴ ሲያደርግ አመታዬቱ፤ ብዙዎችን ካሳዘነ ውሎ አድሯል።

No comments:

Post a Comment