Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 22, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት እንደምትቀበለው አስታወቀች

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መመረጥና የክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን መመረጣቸውን በማስመልከት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕ/ት ቤት ያስተላለፈችው መልክት” በሚል ርእስ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ለአቶ መለስ ዜናዊ አመራር የነበራትን አድናቆትም ገልጣለች።


ቤተክርስቲያኑዋ ” ይህ ያለፈው ዘመን ለአገራችንና ለአፍሪካ ብሎም ለአለም ህዝብ ትልቅ ሚና የነበራቸውን ሁሉ ታላቅ መሪዎች ያጣንበት ዘመን በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ትልቅ ሀዘን ሆኖ ሰንብቷል።” ብላለች።

ቤተክርስቲያኑዋ በመያያዝም ” የህዝባችንን የልማት አንድነት ያጠናከረውና የመንግስታችንን ፖሊሲ በቁርጠኝነት ለማስፈጸም ቀን ከሌሊት ውድ ጊዜያቸውን ለህዝብ ሲሉ እየሰሩ ያለፉት የህዳሴ ግድቡን በማስጀመር ” አባይን የደፈረ ጀግና” በሚል የተጠሩት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራእይን እውን እንዲሆን ቤተክርስቲያናችን ተከታይ ምእመናንና አገልጋይ ካህናቱን በሜአዝ የጀመረችውን የማሳካት እንቅስቃሴ አሁንም ህዝቧንና ያላትን አቅም በመጠቀም ለተግባራዊነቱ ከመንግስት ጎን እንደ ምትንቀሳቀስና መንግስት ድህነትን ታሪክ ለማድረግ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች” በማለት ገልጣለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዛሬም እንደጥንቱ ከመንግስት ጋር በቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጁ ናት በማለት አቋማን ገልጣለች። በሌላ ዜና ደግሞ አልጀዚራ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ጠቅላይ ሚኒሰትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተሾሙ በማለት ዘግቧል።

ሁለቱም ተሻሚዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባላት አለመሆናቸውን የታዘቡ አንድ የምእራብ ዲፕሎማት ” በአሁኑ ሰአት የፕሮቴስታንት ተከታይ የሆነ ወላይታ እና ሙስሊም የሆነ አማራ በከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች ላይ ማየት ያስገርማል” ብለዋል።

No comments:

Post a Comment