Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, August 8, 2012

ሄላሪ ክሊንተን “ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሄላሪ ክሊንተን በሰሞኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ፦_“ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ።

ሰሞኑን ወደ ሰባት የ አፍሪቃ አገሮች ጉዞ ያደረጉት ሄላሪ ክሊንተን በሴኔጋሉ ጉብኝታቸው ባደረጉት ንግግር  የ አፍሪቃ አገሮች ለዲሞክራሲ እና ለ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መረጋገጥ ከመስራት ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው  በማሣሰብ፤ሌላ አጋር ፍለጋ  ባልሆነ መንገድ እየሄዱ ያሉት ከዚህ ተጠያቂነትለማምለጥ  እንደሆነ በማብራራት ወቅሰዋል።


ክሊንተን በዚሁ ጉብኝታቸው ቻይና በኢንቨስትመንት ስም   የአፍሪቃን ሀብት በስፋት እየዘረፈች እንደሆነም የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል። <ዡንዋ> የተሸኘው የቻይና ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፤ሒላሪ ክሊንተን በአፍሪካ  አገሮች እያደረጉ  ባሉት ጉብኝት ቻይናን አስመልክቶ ያደረጉት ንግግር ፤ የቻይና መንግስትን አስቆጥቷል።

“ሒላሪ ክሊንተን ስለአፍሪካ ዕውነታ ባዕድ  ናቸው፤ አለያም  ላለማወቅ ሆነ ብለው  ጆሮሯቸውን ደፍነዋል” ያለው  የቻይና መንግስት፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ንግግር በቻይና እና በአፍሪቃ ግንኙነት መካከል ክፍተት በመፍጠር የአሜሪካን  ጥቅም ለማራመድ ካለመ  ራስ ወዳድነት የመነጨ ነው” ብሏል።

የሄላሪ ክሊንተንን ንግግር፦” እውነታን ያላገናዘ፣ ተራ እና  ስውር አጀንዳ ያለው” በማለት ያጣጣለው  የቻይና መንግስት፤  ቻይና አፍሪካ ውስጥ ለልማትና ለኢንቨስትመንት  ቢሊዮን  ዶላሮች ማፍሰሷንና  የአፍሪካ ዋነኛ አጋር መሆኗን  ጠቅሷል::

ሂላሪ ክሊንተን በቻይና ላይ የዚህ ዓይነት ወቀሳ ሢሰነዝሩ የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም። ከዓመት በፊት በተመሠሳይ በአፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት፤ ቻይና በኢንቨስትመንት ስም  የአፍሪካን ሀብት እና ርካሽ ጉልበት  እየበዘበዘች እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment