Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, June 29, 2012

ስቴት ዲፓርትመንት እስረኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት ዜና:-ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የአቶ መለስ መንግስት ከመላው ዓለም ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተነሱበት ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት በተከሰሱ 24 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በ አቶ መለስ መንግስት ላይ ከ ዓለም ዙሪያ ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው።

በፍርድ ቤቱ ብይን ላይ ተቃውሞ ካሰሙት መካከል አንዱ፤ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ነው።የዩ.ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት ፤ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የኢትዮጵያ ያ ፍርድ ቤት ያሳለፈው የጥፋተኝነት ብይን እጅግ እንደሚያሳስበው በመጥቀስ፤ ውሳኔው በኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ህግ ይዘት እንዲሁም፤ አገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ዋስትና በሰጠቻቸው፤ በፕሬስ እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አተገባበር ዙሪያ ከባድ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብሏል።


የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ቪክቶሪያ ኑላንድ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የጋዜጠኞች መታሰር ሚዲያዎች እንዳያብቡና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዳይዳብር ያለው ተጽዕኖ ከባድ መሆኑን በማመልከት፤ከኢ ትዮጵያ ጋር የሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በነበረን ውይይት፦ ሀሳብን የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነትን ማረጋገጥ፤ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ እንደሆነ አቋማችንን ግልጽ አድርገንላቸዋል ብለዋል።

“ነፃ ሚዲያው በጥቃት ስር ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ፤የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በጭቆና ስር ናቸው”በማለት ሄላሪ ክሊንተን መናገራቸውን ያወሱት የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባዩዋ፤ለዚህም ነው ዩናይትድ ስቴትስ በየትኛውም የዓለማችን ክፍሎች የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥሪ የምታቀርበው”ብለዋል።

ዓለማቀፎቹ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ ለተመሰረተው ክስ ያሳለፈውን የጥፋተኝነት ብይን በማውገዝ፤ መንግስት ክሱን በአስቸኳይ ውድቅ በማድረግ እስረኞቹን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈታ ጠይቀዋል። 

የጥፋተኝነት ብይን የተላለፈበትን ዕለትም፦” ይህ ለኢትዮጵያ ፍትህ ፤የጨለማ ቀን ነው” ሲል ነው አምነስቲ የገለጸው። ዘ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር እንደዘገበው ደግሞ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን በኢትዮጵያ ላይ ዓለማቀፍ ውግዘትን እያስከተለ ነው። እንደ ክርስቲያን ሞኒተር ዘገባ ፤የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት አባል የሆኑት ሴናተር ፓትሪክ ሌሂ፤ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ወታደራዊ እርዳታ እንዲቆም ጠይቀዋል።

በተለይ አሜሪካ በሚቀጥለው ዓመት ለኢትዮጵያ ለመስጠት ያሰበችው 500 ሺህ ዶላር፤ የአቶ መለስ መንግስት ለፕሬስ ነፃነት በሚሰጠው ክብር እየታዬ ውሳኔ ሊሰጠው እንደሚገባ፤ ሴናተር ሌሂ አሣስበዋል። ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ኮሚቴ(ሲፒጄ) በበኩሉ በእስክንድር እና ስደት ላይ ባሉ አምስት ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤት ብይን ተቀባይነት ማግኘቱን አምርሮ በመኮነን፤ የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ-ሽብር ህጉን ፦ ነፃ ሀሳብን ለማፈኛ እየተጠቀመበት ነው” ብሏል።

ለጋሽ አገሮች በ እነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን ብይን እንዲያወግዙ እንዲሁም ኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ህጓን ታሻሽል ዘንድ ጫና እንዲያደርጉ ሲፒጄ ጠይቋል። “እኛ ፔን፤ ዓለማቀፉ ህብረተሰብ፦ ከእስክንር ነጋ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በትግል ላይ ካሉት እና አገራቸውን ጥለው ከተሰደዱት 150 የ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጎን እንዲቆም እንጠይቃለን” ያለው ደግሞ ፔን አሜሪካን ሴንተር ነው።
የፔን አሜሪካ ሴንተር ፕሬዚዳንት ፒተር ጎድዊን በዚሁ መግለጫቸው ለጋዜጠኛ እስክንድር ባስተላለፉት መልዕክት፦”እስክንድር፤ከእስር ተለቀህ በነፃነት እስከምትራመድ ድረስ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል። ጋዜጠኛ እስክንርድር ነጋ ከወራት በፊት የፔን ባርባራ ጎልድ ስሚዝ የመፃፍ ነፃነት ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል።

ቢቢሲ፣ ሮይተርስ፣አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ አሶሲየትድ ፕሬስ፣ዘጋርዲያን እና ሌሎች እጅግ በርካታ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የተመሰረተውን የሽብርተኝነት ክስ ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤት፤ በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።

የሁሉም ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ በተከሳሾች ላይ በተላለፈው ብይን ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ተቋማት እና በለጋሽ አገሮች ባለስልጣናት ተቃውሞ፤ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ነው። ቀደም ሲል በሌለበት የተፈረደበትን ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌን ጨምሮ በተመሳሳይ አምስት ጋዜጠኞች በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ መባላቸው እና ከባድ የ እስር ቅጣት መቀበላቸው አይዘነጋም።

በመሆኑም ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፐርሰን፤ እንዲሁም የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ መምህርት ርዕዮት ዓለሙ እና የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው እስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment