Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, May 22, 2012

ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ የፈለጉ ኢትዮጵያውያን ቪዛ እየተከለከሉ ነው

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ወደ  ኢትዮጵያ ሄደው ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ የፈለጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን፦”የግንቦት 7 አባላት ናችሁ” እየተባሉ በየ አገራቱ ባሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እየተከለከሉ ነው። በቤልጂዬም የምትኖር እና ስሟን መግለጽ ያልፈለገች አንዲት ኢትዮጵያዊ ሰሞኑን ወደ አገሯ አቅንታ ዘመዶቿን ለመጠየቅ ብትፈልግም፤በብራሰልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፦”የግንቦት ሰባት አባል  ስለሆንሽ ቪዛ አንሰጥሽም” በማለት ከልክሏታል።

ኤምባሲው  ለአክቲቪስቷ የግንቦት ሰባት አባልነት የጠቀሰውና ያቀረበው ማስረጃ  በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያውያን ባካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎች ላይ መሳተፏን ነው። እንዲሁም  በፍራንክፈርት፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሌሎች የ አውሮፓ እና የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት ለመሄድ ፈልገው ከየኤምባሲዎች  ተመሣሳይ ምላሽ ተሰጥቷቸው ቪዛ መከልከላቸውን ተናግረዋል።

የአቶ መለስ መንግስት ፦”የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ህገ-መንግስታዊ መብት ነው” የሚል ህገ መንግስት ያረቀቀና ያጸደቀ ቢሆንም፤በተግባር እየተከተለ ያለው አገዛዝ፦”ንጉስ አይከሰስ፤ሰማይ አይታረስ” በሚል ያረጀ ብሂል የሚመራ  እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፦”የ ኢትዮጵያ ህገ-መንግስት የተፃፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ አላወጣም”ማለታቸው አይዘነጋም።


No comments:

Post a Comment